መከላከያ ከ ሀዲያ ሆሳዕና – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

መከላከያ 2-1 ሀዲያ ሆሳዕና
33′ በሃይሉ ግርማ 79′ ቴዎድሮስ በቀለ | 61′ ሀይደር ሸረፋ


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በመከላከያ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
82′
መሃመድ ናስር ወጥቶ ካርሎስ ዳምጠው ገብቷል፡፡

ጎልልል!!! መከላከያ
79′ ቴዎድሮስ በቀለ ከቅጣት ምት ግሩም ግብ አስቆጥሮ መከላከያን በድጋሚ መሪ አድርጓል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሀዲያ ሆሳዕና
77′
ተመስገን ገብረፃድቅ ወጥቶ አሸናፊ አደም ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሀዲያ ሆሳዕና
75′
ሀይደር ሸረፋ ወጥቶ እንዳለ ደባልቄ ገብቷል፡፡

72′ ሀዲያ ሆሳዕና በ2ኛው አጋማሽ የተለየ ሆኖ ቀርቧል፡፡ በተደጋጋሚ የመከላከያን የተከላካይ መስመር በመፈተሽ ላይ ይገኛሉ፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
70′
በሃይሉ ግርማ ወጥቶ ኡጉታ ኦዶክ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
68′
ሳሙኤል ሳሊሶ ወጥቶ ማራኪ ወርቁ ገብቷል፡፡

ጎልልል ሀዲያ ሆሳዕና
61′ ከተመስገን የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ሀይደር ሸረፋ ሀዲያን አቻ የምታደርግ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

57′ አምራላ ደልታታ የመታው ኳስ የግቡን ቋሚ ታኮ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሀዲያ ሆሳዕና
56′
መስቀሌ መንግስቱ ወጥቶ ቢንያም ታዬ ገብቷል፡፡

53′ ተመስገን ከግብ ጠባቂው ፊት ለፊት ጥሩ የግብ ማስቆጠር አጋጣሚ አግኝቶ በግቡ አናት ወደ ላይ ሰዶታል፡፡

48′ ሳሙኤል ሳሊሶ ከቅጣት ምት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በመከላከያ መሪነት ተጠናቋል፡፡

45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

ጎልልል!!!! መከላከያ
33′ በሃይሉ ግርማ ከሳጥን ውጪ በጥሩ ሁኔታ የመታት ኳስ መረብ ላየይ አርፋለች፡፡

30′ መሃመድ ናስር የዳኛን ውሳኔ በመቃወም የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

29′ ሳሙኤል ታዬ ፍፁም ቅጣት ምተት ክልል ውስጥ በግራ እግሩ የመታውን ኳስ ሙሴ አድኖበታል፡፡ አደገኛ ሙከራ ነበር፡፡

25′ ፍሬው ሰለሞን ተጫዋቾችን አልፎ ሳጥን ውስጥ ከገባ በኋላ ያቀበለውን ኳስ ሳሙኤል ታዬ ሞክሮ ሙሴ ይዞበታል፡፡

25′ ጨዋታው የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እየታየበት ነው፡፡ ሀዲያ ሆሳዕናዎች ወደ ግብ በመድረስ ከባለሜዳዎቹ ተሽለዋል፡፡

ቢጫ ካርድ
15′
አዲሱ ተስፋዬ የመጀመርያውን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

13′ ሀድያ ሆሳዕናዎች ግብ ቢያስቆጥሩም ከጨዋታ ውጪ ተብሎ ሳይፀድቅ ቀርቷል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በመከላከያ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የመከላከያ አሰላለፍ

1 ጀማል ጣሰው

2 ሽመልስ ተገኝ – 16 አዲሱ ተስፋዬ – 29 ሙሉቀን ደሳለኝ – 3 ቴዎድሮስ በቀለ

10 ፍሬው ሰለሞን – 21 በሃይሉ ግርማ – 13 ሚካኤል ደስታ

9 ሳሙኤል ሳሊሶ – 17 መሃመድ ናስር – 19 ሳሙኤል ታዬ

ተጠባባቂዎች
22 ይድነቃቸው ኪዳኔ
20 ሚልዮን በየነ
7 ማራኪ ወርቁ
6 ታፈሰ ሰርካ
26 ኡጉታ ኦዶክ
12 አቤል ከበደ
11 ካርሎስ ዳምጠው


የሀዲያ ሆሳዕና አሰላለፍ

1 ሙሴ ገብረኪዳን

6 ታረቀኝ ጥበቡ – 4 ውብሸት አለማየሁ – 28 እርቅይሁን ተስፋዬ – 17 ሄኖክ አርፊጮ

12 ዱላ ሙላቱ – 22 አድናን ቃሲም – 5 መስቀሌ መንግስቱ – 8 ሀይደር ሸረፋ – 14 አምራላ ደልታታ

9 ተመስገን ገብረፃድቅ

ተጠባባቂዎች
29 ኄኖክ ወንድማገኝ
19 አየለ ተስፋዬ
21 አልፋየሁ ሙላቱ
25 ኢማኑኤል አኪራሺ
10 ቢንያም ታዬ
13 አሸናፊ አደም
18 እንዳለ ደባልቄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *