የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ጥር 23 ይጀምራል

የ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ውድድር በመጪው ጥር 23 እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

ፌዴሬሽኑ ባወጣው ድልድል ባለፉት ጥቂት አመታት እንደነበረው ሁሉ በዚህኛውም ውድድር ላይ የሚካፈሉት 16ቱ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ብቻ ናቸው፡፡

በድልድሉ መሰረት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና የመጀመርያውን ዙር የማይጫወቱ ሲሆን ሁለቱ ቡድኖች እስከ ፍፃሜው ጨዋታ ድረስ አይገናኙም፡፡ የአምናው ቻምፒዮን ደደቢት በበኩሉ የፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታውን ጥር 24 ከሀዋሳ ከነማ ጋር ካካሄደ ከ4 ቀናት በኋላ በድጋሚ ሀዋሳን ይገጥማል፡፡

ድልድሉ ይህንን ይመስላል ፡-

1ኛ ዙር

ጨዋታ 1 ፡ ሙገር ሲሚንቶ ከ አርባምንጭ ከነማ (23/05/2007)

ጨዋታ 2 ፡ ሲዳማ ቡና ከ ወልድያ (23/05/2007)

ጨዋታ 3 ፡ ዳሽን ቢራ ከ መከላከያ (28/05/2007)

ጨዋታ 4 ፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ኤሌክትሪክ (30/05/2007)

ጨዋታ 5 ፡ አዳማ ከነማ ከ ወላይታ ድቻ (30/05/2007)

ጨዋታ 6 ፡ ሀዋሳ ከነማ ከ ደደቢት (28/05/2007)

 

2ኛ ዙር

ጨዋታ 7 ፡ ቅዱሰ ጊዮርጊስ ከ ጨዋታ 1 አሸናፊ

ጨዋታ 8 ፡ የጨዋታ 2 አሸናፊ ከ ጨዋታ 3 አሸናፊ

ጨዋታ 9 ፡ የጨዋታ 4 አሸናፊ ከ ጨዋታ 5 አሸናፊ

ጨዋታ 10 ፡ ኢትዮጵያ ቡና ከ ጨዋታ 6 አሸናፊ

ግማሽ ፍፃሜ

ጨዋታ 11 ፡ ጨዋታ 7 ከ ጨዋታ 8

ጨዋታ 12 ፡ ጨዋታ 9 ከ ጨዋታ 10

 

ፍፃሜ

የጨዋታ 11 አሸናፊ ከ ጨዋታ 12 አሸናፊ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *