ቅዱስ ጊዮርጊሰ ብሪያን ኡሞኒን በይፋ አስፈረመ

የ2015 የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዩጋንዳዊው አጥቂ ብራያን ኡሞኒን ማስፈረሙን በድረ-ገፁ አስታውቋል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ በድረ-ገፁ የኡሞንኒን መፈረም ያስተወቀው እነዲህ ባለ መልኩ ነው፡፡

ብሪያን ኡሞኒ ፊርማውን ለቅዱስ ጊዮርጊስ አኑሯል

የቀድሞው የካምፓላ ሲቲ ካውንስል፣ ዩንቨርስቲ ኦፍ ፕሪቶሪያ እና የታንዛኒያው አዛም ዩጋንዳዊ አጥቂ ብሪያን ኡሞኒ በጥር ወር በተከፈተው የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት የክለባችን ተጨዋች መሆኑን በፊርማው አረጋግጧል፡፡

እ.ኤ.አ. ታህሳስ 12/1988 ፊራንሲሲ ኬርሚት እና ሎያስ ዋንችንጐ ከተባሉት እናት እና አባቱ ጃንጃ በተባለችው የዮባንደ ሁለተኛ ከተማ የተወለደው ብሪያን ኡሞኒ አራት ልጆች ላሉት ቤተሰብ የመጨረሻ ልጅ ነው፡፡ ለአሁኑ ሰአት ዩጋንዳ ካፈራቻቸው ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ነው፡፡ እየተባለ በመወደስ ላይ የሚገኘው ብሪያን ከ2013 ጀምሮ ለታንዛኒያው እዛም ሲጫወት ቆይቷል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ እግር ኳስ ተንታኞች ኡሞኒ ያለው ፍጥነት፣ ኳስ አገፋፉ ኳስ የማቀበል ስኬቱ ከማይታመን አጨራረሱ ጋር ተዓምር አጥቂውን የተሟላ ተጨዋች ነው ይሉታል፡፡ ከ2009 ጀምሮም በቀድሞ አሰልጣኛችን ስርዲዮቪች ሚሎሰቢች ሜቶ በሚመራው የኡጋንዳ ብሔራዊ ቡድን አባል ነው፡፡ ወላጅ እናቱ በሞት ከተነጠቀ በኋላ ወደ ዋና ከተማዋ ካምፓላ በመሄድ በህፃንነቱ አጐቱ ጋር መኖር የጀመረው ኡሞኒ እግር ኳስን ለመጀመር ረዥም ጊዜን አልወሰደበትም፡፡ እግር ኳስን በህፃንነቱ ይጀምር እንጂ በነበረው ተክለ ሰውነት ምክንያት በትምህርት ቤት ቡድኖች ውስጥ ለመሳተፍ ረዥም ጊዜን ወሰዶበታል፡፡

የብሪያን ኡሞኒ የክለብ ህይወት የጀመረው እ.ኤ.አ በ2007 ካምፓላ ሲቲ ካውንስል በሚባለው ክለብ ውስጥ ነበር፡፡ ለካምፓላ ሲቲ ካውንስል የመጀመሪያ ጨዋታውን ሲያደርግም ተቀይሮ በመግባት በመጀመሪያ ጨዋታው ግብ አሰቆጥሯል፡፡ ለክለቡ መጫወት በጀመረበት አመትም ካምፓላ ሲቲ ካውንስልን ከአስራ አንድ አመት በኋላ የሊጉን ዋንጫ እንዲያገኝ ሲያደርግ እሱም የአመቱ ኮከብ ግብ አግቢ እና ኮከብ ተጨዋች በመሆን አጠናቀቀ፡፡

በሁለተኛው አመት የክለብ ቆይታውም በግሉ የተሳካ አመት ነበረ፡፡ በሊጉ በተጫወታቸው ጨዋታዎች 19 ግቦች አስቆጥሮ የኮከብ ግብ አግቢነት ውድድሩን በሦስት ግቦች ብቻ ተበልጦ በሁለተኝነት አጠናቀቀ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ክለቡ እ.ኤ.አ. በ2009 የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ላይ በጠቅላላ አራት ግቦችን በማስቆጠር ሁለተኛ ዙር እንዲደርስ ከማድረጉም በላይ ግቡን ያስቆጠረው ደግሞ ፊሬቫሪዮ ማፑቶ እና የደቡብ አፍሪካው ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ላይ መሆኑ ደግሞ የተጨዋቹን ስብእና ከፍ ማድረግ ችሎ ነበር፡፡ በዚያኑ አመትም በተከታታይ በተሰለፈባቸው 16 ጨዋታዎች በሙሉ ግብ በማስቆጠሩ ሲምባ፣ ያንጋ፣ አልሂላል፣ ማሜሎዲ ሰንዶውንስ እና ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ በመሳሰሉ ክለቦች እይታ ውስጥ መግባት ቻለ፡፡ በ2009/10 የሳምንት የሙከራ ጊዜን ካሳለፈ በኋላ ሙከራውን በተሳካ ሁኔታ በማለፍ በሁለት አመት የኮንትራት ዘመን የደቡብ አፍሪካውን ሱፐር ስፖርት ዩናይትድን ተቀላቀለ፡፡

ከሱፐር ስፖርት በኋላም ወደ ዩንቨርስቲ ኦፍ ፕሪቶርያ፤ለፖርት ላንድ ቲምበርስ እና ለቬትናሙ ቢንህ ክለብ ከተጫወተ በኋላ በያዝነው ወር በተከፈተው የጥር ወር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስን ተቀላቅሏል፡፡

ስለዝውውሩ ያነጋገርነው ብሪያን ኡሞኒ «በዚህ ክለብ የተጫወቱ እና እየተጫወቱ ያሉ ጓደኞቼ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጥንካሬ በተደጋጋሚ ነግረውኛል፡፡ ለዚህ ታላቅ ክለብ በመፈረሜ ደስታ ተስምቶኛል፡፡አሁን ያለኝን ሁሉ ነገር አውጥቼ በመስጠት በዚህ ክለብ ታሪክ አካል መሆን እፈለጋለሁ» ሲል ለልሳነ ጊዮርጊስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ተናግሯል፡፡

የብሪያንን የአለም አቀፍ ጨዋታዎችን ቁጥሮች ከተመለከትን ኡሞኒ ለዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድንተሰልፎ መጫወት የጀመረው እ.ኤ.አ. በ2008 ነው፡፡ በተለይም መሰለፍ በጀመረበት በመጀመሪያ አመቱ የተካሄደውን እና ዩጋንዳ ለአስረኛ ጊዜ የሴካፋን ዋንጫ ስታነሳ የቡድን አባል የነበረ ሲሆን የውድድሩ ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን አጠናቅቋል፡፡

ብሪያን ኡሞኒ ከእግር ኳስ ውጪ ከኪያምቦ ዩንቨርሲቲ በዲግሪ ተመርቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *