ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ መከላከያ – ቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት

ኢትዮ ኤሌክትሪክ1-2መከላከያ

19′ ኢብራሂም ፎፋኖ | 68′ ቴዎድሮስ በቀለ፣ 90′ ሳሙኤል ታዬ


መከላከያ ባለቀ ሰዐት በሳሙኤል ታዬ አማካኝነት ባስቆጠረው ግብ አማካኝነት ጨዋታውን 2-1 ማሸነፍ ችሏል።


90+4′ የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ

ምንይሉ ወንድሙ ወጥቶ ካርሎስ ዳምጠው ገብቷል።


90+1′ ቴዎድሮስ በቀለ ሰዐት በማባከን ቢጫ ካርድ አይቷል።


90′ ጎል!!!!

ሳሙኤል ታዬ ከቀኝ መስመር በኩል ወደግብ የመታው ኳስ መረብ ላይ አርፏል።


90′ – ተጨማሪ ሰዐት – 4 ደቂቃ


83′ ሙሉዓለም ጥላሁን በግንባሩ የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።


78′ በሃይሉ ግርማ ከ35 ሜትር ርቀት አካባቢ የመታው ኳስ ዒላማውን ሳይጠብቅ ቀርቷል።


68′ ጎል!!!!

ቴዎድሮስ በቀለ ከሳሙኤል ታዬ የተሰጠውን ኳስ ወደግብ በመቀየር መከላከያን አቻ አድርጓል።


65′ ምንይሉ ወንድሙ ከቅጣት ምት የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወደውጪ ወጥቷል።


56′  የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ

ፍፁም ገብረማርያም ወጥቶ ብሩክ አየለ ገብቷል።


50′ አዲስ ነጋሽ በግንባሩ የሞከረው ኳስ የግቡን አግዳሚ ገጭቶ ወጥቷል።


46′ ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል።


የመጀመሪያው አጋማሽ በኢትዮ ኤሌክትሪክ 1-0 መሪነት ተጠናቋል።


45′ ተጨማሪ ሰዓት – 1 ደቂቃ


42′ ኢብራሂም ፎፋኖ ፍፁም ቅጣት ምት ለማግኘት አስመስለህ ወድቀሀል በሚል ቢጫ ካርድ ተመልክቷል።


34′ ሳሙኤል ሳሊሶ ከሳጥኑ ውጪ አክርሮ በመምታት የሞከረውን ኳስ ሱሌማን አቡ እንደምንም ብሎ አውጥቶታል።


33′ ዳዊት እስጢፋኖስ ከርቀት ወደግብ ቢመታም አቤል ማሞ በቀላሉ አድኖታል።


21′ ፍፁም ገብረማርያም ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ ወደግብ የመታውን ኳስ አቤል አውጥቶታል።


19′ ጎል!!!!

ኮትዲቯራዊው አጥቂ ኢብራሂም ፎፋኖ ከአሸናፊ ሽብሩ የተላከለትን ኳስ በመጠቀም ኤሌክትሪክን መሪ አድርጓል።


15′ ጨዋታው በተቀዛቀዘ መንፈስ ቀጥሏል።


5′ ሙሉዓለም ጥላሁን ከሳጥኑ መሃል ላይ አግኝቶ የመታው ኳስ ዒላማውን ሳይጠብቅ ቀርቷል።


4′ ዳዊት እስጢፋኖስ ከቅጣት ምት ያሻማውን አደገኛ ኳስ ግብ ጠባቂው አቤል ማሞ ይዞታል።


1′ ጨዋታው በመከላከያ አማካኝነት ተጀምሯል።


ትናንትና ጠዋት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየው ጀግናው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር የ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።


የመጀመሪያ አሠላለፍ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ

22. ሱሊማን አቡ

11. አወት ገ/ሚካኤል– 21. በረከት ተሰማ — 15. ተስፋዬ መላኩ —  7. አለምነህ ግርማ 

 23. አሸናፊ ሽብሩ — 5 . አዲስ ነጋሽ (አምበል) — 10. ዳዊት እስጢፋኖስ

16. ፍፁም ገ/ማርያም — 18 . ሙሉአለም ጥላሁን —  4.  ኢብራሂም ፎፋኖ


ተጠባባቂዎች

 1 ኦኛ ኦሜኛ

19 ደረጄ ሀይሉ

9 ብሩክ አየለ

17 አብዱልሀኪም ሱልጣን

12 ትዕዛዙ መንግስቱ

2 አቤል አክሊሉ

8 በሃይሉ ተሻገር


የመጀመሪያ አሠላለፍ – መከላከያ

1 አቤል ማሞ

3 ቴዎድሮስ በቀለ — 16 አዲሱ ተስፋዬ — 4 አወል አብደላህ — 2 ሽመልስ ተገኝ

19 ሳሙኤል ታዬ — 21 በሀይሉ ግርማ — 13 ሚካኤል ደስታ — 9 ሳሙኤል ሳሊሶ

7 ማራኪ ወርቁ — 14 ምንይሉ ወንድሙ


ተጠባባቂዎች

22 ይድነቃቸው ኪዳኔ

28 ሚሊዬን በየነ

17 ምንተስኖት ከበደ

11 ካርሎስ ዳምጠው

15 ቴውድሮስ ታፈሰ

23 መስፍን ኪዳኔ

27 ተመስገን ገብረፃድቅ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *