ኢትዮጵያ ቡና 2-1 ሀዋሳ ከተማ | የአሰልጣኞች አስተያየት 

ገዛኸኝ ከተማ- ኢትዮጵያ ቡና

“የጨዋታው እንቅስቃሴ ጥሩ ነበር፤ ሁለታችንም ጥሩ ተጫውተናል። ባሳለፍነው ሳምንት ነጥብ በመጣላችን የተነሳ ጫና ውስጥ ሆነን ነበር የተጫወትነው፡፡ ከዛ ጫና ለመውጣት ይህ ውጤት ያስፈልገን ነበር ያም ተሳክቶልናል፡፡”

 

የተከላካይ መስመር ስህተት

“እየተስናገዱብን ኳሉ ኳሶች ላይ በመመስረት ስራዎችን ለመስራት እየሞከርን ነው፡፡ ከዚህ ቀደም አይታችሁ ከነበረ በርካታ የግብ እድሎችን ፈጥረን የምናመክንባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ አሁን እነዛን እየቀረፍን ወደተሻለ መንገድ እየመጣን ነው፡፡”

 

ስለተወሰደባቸው ብልጫ

” ሀዋሳ ቀላል የሚባል ቡድን አይደለም ፤ ተፎካካሪ ቡድን ነው ፤ የነበራቸውን የኳስ ብልጫ ለመቀነስ የተቻለንን በማድረግ መጠቀም የሚገቡንን ክፍተቶች በመጠቀም ወደ እነሱ ክልል በመግባት የተሻለ ነገር ለመፍጠር ጥረት አድርገናል ፤ ያንንም አሳክተናል ማለት ይቻላል፡፡

 

83ኛው ደቂቃ ላይ ስለተፈጠረው ክስተት

” እኛ ከውጪ እንደመሆናችን ውሳኔ መስጠት የሚችለው ዳኛው ነው፤ እኛም

የክስተቱን ቪድዮ ከተመለከትን በኃላ የሚሆነውን እናያለን፡፡”

 

በተጠባባቂ ወንበር ላይ ይታይ ስለነበረው አለመረጋጋት

“ይሄ ነገር ሊሆን የቻለው ውጤትን ከመፈለግና ከነበረብን ጫና ተነተርሶ የመጣ ስለሆነ በቀጣይ ለማስተካከል እንጥራለን፡፡”

ውበቱ አባተ- ሀዋሳ ከተማ

ስለ ጨዋታው

” በእንቅስቃሴ ደረጃ ከተመለከትነው ለኛ መጥፎ የሚባል አይደለም ፤ በፈጠርናቸው ጥቃቅን የሚባሉ ክፍተቶች ጨዋታውን እንዳንቆጣጠር አድርገውናል፡፡ ጎል ያስተናገድናባቸው መንገዶች በተለይ በጣም ቀላል በሚባል መንገድ ነው ፤ 2-0 ተመርተህ ከዛ ለመመለስ ብዙ ታግለናል ነገርግን ከአቅማችን በላይ ነበር፡፡”

 

በጨዋታው ስለነበራቸው የኳስ ቁጥጥር ብልጫ

” በኳስ ቁጥጥር ተሻልን ነበርን፡፡ ነገርግን የመጨረሻው የሜዳ ክፍል ላይ ስንደርስ በተጫዋቾቼ ላይ መቻኮል ይታይ ነበር ከዚህም በተጨማሪ በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ ከአማካዮቻችን ብዙ እገዛ አልተደረገልንም ፤ ይህም ነገር ብዙ የጎል እድሎችን እንዳንፈጥር አድርጓናል ከዛ ውጪ ግን በተለይ ዳንኤል ደርቤ ከጉዳት እና ቅጣት ነው የተመለሰው እንደዚሁ መላኩ ጎሉ ሲቆጠር ተጎድቶ ከሜዳ ውጪ ነበር የነዚህ ልጆች የማች ፊትነስ ላይ አለመገኘት አስተዋፆ ነበር ፤ ስህተት ነበረብን ብዩ የማስበው ፊት እና ከኃላ መስመር ላይ መጠነኛ ክፍቶች ነበሩብን፡፡ ከዚያ ውጪ እነሱም ከነበሩት ጫና አንጻር ባልተጠበቅናቸው መልኩ ተንቀሳቅሰዋል ከዚያ በተጨማሪ ዛሬ ሜዳ ላይ ከገጠምነው ኢትዮጵያ ቡና ይልቅ ከባድ የነበረው የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ነበር፡፡”

ስለ ቡድኑ የአጠቃላይ የአመቱ እንቅስቃሴ

“ሀዋሳ ዘንድሮም ብቻ ሳይሆን አምናም ጥሩ ሜዳ ስናገኝ ጥሩ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ አለን፡፡ ምናልባት ከሲዳማ ጋር በተደረገው ጨዋታ ብቻ ነው በእንቅስቃሴም በውጤትም ጥሩ ያልነበርንበት ጨዋታ፡፡ ነገርግን ከዚያ ውጪ ቡድኑ በቡድን የእንቅስቃሴ ችግር የለበትም፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *