ወልድያ 0-0 ድሬዳዋ ከተማ | የአሰልጣኞች አስተያየት

ንጉሴ ደስታ – ወልድያ

” በዚህ ታሪካዊ ስታድየም አሸንፈን ለመውጣት ከፍተኛ ፍላጎት ነበረን፡፡ ሆኖም የዕለቱ ዳኛ ጨዋታውን አበላሽቶብናል። በእንቅስቃሴ ረገድ ጥሩ ነበርን። እንደምታዩት ከፍተኛ የሆነ የአጨራርስ ችግር አለብን ፤ ማሸነፍ የሚገቡንን ጨዋታ ነጥብ እየተጋራን በመውጣት ዋጋ እየፈልን ነው። በቀጣይ ወደ ገበያው በመውጣት የአጥቂ ችግራችንን ለማስተካከል እንሞክራለን፡፡ ”

ስለ ሜዳው

“ምን ማለት ይቻላል ፤ እንደምታየው ነው፡፡ የህዝቡ ድባብ እንኳን ገብተው ለሚጫወቱት ለኔ አሰልጣኙ እንኳን የፈጠረብኝ ስሜት ከባድ ነው፡፡ እንደነዚህ ያሉ ስታድየሞች በተለያዩ የኢትዮዽያ ክልሎች ቢሰሩ ጥሩ የሆነ ጨዋታ ማየት እንችላለን። ”

ዘለለም ሽፈራው – ድሬዳዋ ከተማ

” ጨዋታው ጥሩ ነበር። ጨዋታው ምንያህል የአጥቂ ችግር እንዳለብን አሳይቷል፡፡ በእርግጥ እስካሁን ጎል ብዙ አለማስቆጠራችን አጥቂዎቻችን ላይ ጫና ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸው ይሆናል፡፡ በተለይ ዛሬ ለረጅም ደቂቃ አንድ ተጨዋች በቀይ ወጥቶልን ጎል አለማስቆጠራችን የአጥቂ ችግር እንዳለብን ግልፅ ማሳያ ነው፡፡ መሀል ላይ ኳስ ማሸራሸር አይደለም ጎል የሚሆነው።  የአጨራረስ እና የአጥቂ ችግራችንን በቶሎ ማስተካከል ይጠበቅብናል ። የነበረው ድባብ ግን ጥሩ ነበር፡፡ “

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *