ሀዋሳ ከተማ ከሱዳን ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር ዛሬ 10:00 ላይ በአዲስ አበባ ስቴዲዮም የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል።
የወዳጅነት ጨዋታ የግብዣ ጥያቄውን ያቀረበው የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ሲሆን ሀዋሳ ከተማ ወደ ሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ከመግባቱ በፊት ራሱን ለመመልከት ይህ የወዳጅነት ጨዋታ በሚገባ እንደሚረዳው በማመን ለመሳተፍ እንደፈለገ ለማወቅ ተችሏል
ሀዋሳ ከተማ በመጪው እሁድ አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ ከ አአ ከተማ ጋር የ2ኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡