የብሄራዊ ቡድኑ ህክምና ባለሙያ ዶ/ር አያሌው ጥላሁን ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለ ቡድኑ አጠቃላይ የጤንነት ፣ የስነ-ልቡና እና የጉዳት ሁኔታ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
ዶ/ር አያሌው በልምምድ ወቅት ጉዳት ስላጋጠማቸው ተጫዋቾች በተናገሩት መሰረት ስዩም እና በኃይሉ ለነገው ጨዋታ ብቁ ናቸው፡፡
‹‹ በኃይሉ በሳምንቱ መጀመርያ ነበር ጉዳት የደረሰበት፡፡ ቁርጭምጭሚቱ ላይ መጠነኛ ጉዳት ቢደርስበትም 1 ቀን ብቻ ነው ልምምድ ያለፈው፡፡ ስለዚህ ለእሁዱ ጨዋታ ብቁ ነው፡፡
‹‹ አቤል ማሞ ደግሞ ትናንት ነው የተጎዳው፡፡ መዳፉ ላይ ቀለል ያለ ጉዳት ከመድረሱ ውጪ አጥንቱ ላይ የተከሰተ ከባድ ጉዳት አልተስተዋለም፡፡ ቢሆንም የመሰለፍ እና ያለመሰለፉን ጉዳይ የምናውቀው ነገ ይሆናል፡፡
‹‹ ስዩም ተስፋዬም ቀላል ግጭት ነው የደረሰበት፡፡ ከጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ በማገገሙ መቶ በመቶ ለጨዋታው ብቁ ሆኗል፡፡ ›› ብለዋል፡፡