​የፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች የሚሳተፉበት የፉትሳል ውድድር ዛሬ ተጀምሯል

ራዕይ ያለው ወጣት እናፍራ የፉትሳል ማህበር የሚያዘጋጀው ውድድር ለ11ኛ ጊዜ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡

ከ1999 ጀምሮ በየአመቱ በክረምት ወራት የሚካሄደው ይህ የፉትሳል ውድድር ዘንድሮም ለ11ኛ ጊዜ ከሐምሌ 22 – ነሐሴ 14 ድረስ በሁለት ምድብ ተከፍሎ በአስር ቡድኖች መካከል የሚካሄድ ይሆናል። በኮተቤ ሚትሮፖሊታን ዩንቨርሲቲ እና ሰላም ህፃናት መንደር ሜዳም ጨዋታዎቹ ይከናወናሉ።

ምድብ ሀ

አቤም ሆቴል ፣ ገርጂ ኢንቲ ስቱዲዮ ፣ ሳሚና ጓደኞቹ ፣ በረከትና ጓደኞቹ ፣ ፔኬ

ምድብ ለ

mk የፊኒሺንግ ሥራ ፣ ቤተሰብ ፣ ተስፋሚካኤል ግሮሰሪ ፣ ቦሌ ፣ ፀሐይ ሮቪሊ

መርሀግብሩ ዛሬ ጠዋት ረፋድ ላይ በምድብ ሀ በሚገኙ ቡድኖች መካከል ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ሜዳ ላይ ሲካሄድ በረከት እና ጓደኞቹ አቤም ሆቴልን 6-3 አሸንፏል፡፡ ገርጂ አንቲ ስቱዲዮ ከ ሳሚ እና ጓደኞቹ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ 9-9 አቻ ተጠናቋል፡፡

ውድድሩ ነገ ይቀጥልና 03:00 ላይ MK የፊኒሺንግ ስራ ከ ቦሌ ፤ 04:30 ላይ ቤተሰብ ከ ተስፋ ሚካኤል በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ ሜዳ የሚካሄድ ይሆናል።

ባለፉት አመታት በተካሄዱ በዚህ የፉትሳል ውድድሮች ላይ በርከት ያሉ ወጣቶች ሲሳተፉበት የቆዩ ሲሆን በኢትዮዽያ የእግር ኳስ ሊግ ውድድሮች ውስጥ እየተጫወቱ የሚገኙ ተጨዋቾችም ሲሳተፉ ቆይተዋል፡፡ በዘንድሮ አመትም እንደ መስኡድ መሐመድ ፣ ምንያህል ተሾመ ፣ ቢኒያም አሰፋ ፣ በረከት ሳሙኤል እና ሌሎችም የሚጫወቱበት ውድድር ይሆናል።

በዚህ ፉትሳል ውድድር ላይ ስም ያላቸው ተጨዋቾች ተሳታፊ መሆናቸውን ተከትሎ በርካታ ተመልካቾች በሜዳዎቹ በመገኘት ጨዋታዎቹን ይከታተሉታል ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *