​ሲሳይ ባንጫ አርባምንጭ ከተማን ተቀላቀለ

በዝውውር መስኮቱ ዝምታን መርጦ የቆየው አርባምንጭ ከተማ የክረምቱን የመጀመርያ ፊርማ በማጠናቀቅ ሲሳይ ባንጫን የግሉ አድርጓል፡፡

የ2003 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ ጠባቂ ተብሎ የተመረጠው ሲሳይ የተጠናቀቀውን የውድድር አመት በአዳማ ከተማ ጀምሮ በአመቱ አጋማሽ በውሰት ወደ ጅማ አባ ቡና አምርቶ ጀማል ጣሰው ከጉዳት ከሜዳ በራቀባቸው ጨዋታዎች እና በጥሎ ማለፉ ውድድር የመለያ ምቶች ላይ ተቀይሮ በመግባት ቡድኑን አገልግሏል፡፡ አሁን ደግሞ በአንድ አመት ኮንትራት ክለቡን መቀላቀል ችሏል፡፡
ጸጋዬ ኪዳነማርያምን አሰልጣኝ አድርጎ የሾመው አርባምንጭ የግብ ጠባቂው ጽዮን መርዕድ እና የአማካዩ አስጨናቂ ጸጋዬን ኮንትራት አድሷል፡፡ የክለቡ አብዛኛው ተጫዋቾች ቀሪ ኮንትራት ያላቸው በመሆኑ በዝውውር መስኮቱ በስፋት ከመሳተፍ የተቆጠበ ሲሆን የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝም ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *