ወልዋሎ ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በዝውውር መስኮቱ በስፋት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርሟል፡፡

በረከት ተሰማ ክለቡን መቀላቀሉ የተረጋገጠ ተጫዋች ነው፡፡ በረከት በኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ2004 ጀምሮ የቆየ ሲሆን የቡድኑ ሁለተኛ አምበል ሆኖ እስከጠናቀቀው የውድድር አመት ክለቡን አገልግሎ ኮንትራቱን በማገባደዱ ወደ ወልዋሎ አምርቷል፡፡

ወግደረስ ታዬ ክለቡን የተቀላቀለ ሌላኛው ተጫዋች ነው፡፡ ወግደረስ በ2007 የብሔራዊ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር ላይ ለሼር ኢትዮጵያ ባሳየው መልካም አቋም ወደ ደደቢት ማምራት ቢችልም በክለቡ የሁለት አመት ቆይታው የተጠበቀውን ያህል አገልግሎት ሳይሰጥ በመጨረሻም ወደ ቢጫ ለባሾቹ አምርቷል፡፡

ወልዋሎ የሶስቱን ዝውውር ጨምሮ እስካሁን ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ቁጥር 9 የደረሰ ሲሆን የቁልፍ ተጫዋቾቹን ውልም እያራዘመ ይገኛል፡፡ እንየው ካሳሁን እና ብሩክ አየለ ከክለቡ ጋር የተስማሙ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት በይፋ ኮንትራት በመፈረም የወልዋሎ ዝውውራቸውን ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *