ዱላ ሙላቱ ለመቐለ ከተማ ፈረመ

መቐለ ከተማ ያለፉትን 4 አመታት በሀዲያ ሆሳዕና ያሳለፈው ዱላ ሙላቱን በእንድ አመት ውል አስፈርሟል፡፡

የመስመር አጥቂው ሀዲያ ሆሳዕና ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ከፍተኛውን ሚና ከተጫወቱት መካከል ግንባር ቀደሙ እንደነበር የሚታወሰ ሲሆን በሊጉ ቆይታውም በግሉ ጥሩ ተንቀሳቅሷል፡፡ ዘንድሮም ከክለቡ ጋር ወደ ፕሪምየር ሊግ ለመመለስ ተቃርቦ በመጨረሻ ጨዋታ በመቐለ ከተማ ተሸንፈው ሳይሳካ መቅረቱ ይታወሳል፡፡

አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት በክረምቱ 6 ተጫዋቾችን ያስፈሰሙ ሲሆን ከዱላ በፊት ጫላ ድሪባ መ ሙሴ ዮሀንስ ፣ ታደለ ባይሳ ፣ አንተነህ ገብረክርስቶስ እና ዳንኤል አድሀኖም መቐለ የደረሱ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *