ዮናስ ገረመው ወደ ጅማ ከተማ አምርቷል

አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ክለብ ጅማ ከተማ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዮናስ ገረመውን የግሉ አድርጓል፡፡

ዮናስ በአመቱ መጀመርያ አንድ የውድድር ዘመን ያሳለፈበት ድሬዳዋ ከተማን ለቆ ወደ ንግድ ባንክ በማምራት ሌላ አንድ የውድድር አመት አሳልፎ ወደ ጅማ ከተማ በአንድ አመት ኮንትራት አምርቷል፡፡

ጅማ ከተማ በክረምቱ 7 ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን ከዮናስ በፊት ኄኖክ አዱኛ ፣ ይሁን እንደሻው ፣ አሸናፊ ሽብሩ ፣ ቢኒያም ሲራጅ ፣ አሚኑ ሰኢድ ፣ ሳምሶን ቆልቻ እና እንዳለ ደባልቄ ለክለቡ የፈረሙ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *