የሴቶች ዝውውር ፡ አዲስ አበባ ከተማ 6 ተጫዋቾችን አስፈረመ

ባሳለፍነው የውድድር ዘመን የተቋቋመውና ልምድ ባላቸው ተጫዋቾች የተዋቀረው አዲስ አበባ ከተማ የሴቶች ቡድን በለቀቁበት ተጫዋቾች ምትክ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ ይገኛል፡፡

አሰልጣኝ የኔነህ ንጋቱ እንደነ ቱቱ በላይ ፣ ቅድስት ቦጋለ ፣ ተራማጅ ተስፋዬ ፣ ሰላም ላዕከ ፣ ስርጉት ተስፋዬ ፣ አስናቀች ወርቁ እና ሳሳሁልሽ ኃይለ ማርያም ክለቡን ለቀው ወደ ሌሎች ክለቦች ማምራታቸውን ተከትሎ ቡድናቸውን ለማጠናከር ስድስት ተጫዋቾችን እስካሁን ማስፈረማቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በሴቶች ፕሪምየር ግ ሁለተኛ ዲቪዝዮን የሚወዳደረው አዲስ አበባ ከተማ የቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ አምበል የነበረችው አማካይዋ ማህሌት ታደሰን እና የቡድን አጋሯ የነበረችው እድላዊት ለማን ጨምሮ ምህረት ኃይሉ እና ስንታየሁ ታፈረን ከጥረት ኮርፖሬት ፣ ትዕግስት ሲሳይን ከድሬደዋ ከተማ እንዲሁም ፀጋ ንጉሴን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ማስፈረም ችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *