ቢኒያም በላይ በአቋም መለኪያ ጨዋታ ግብ አስቆጥሯል

ኢትዮጵያዊው አማካይ ቢኒያም በላይ ስኬንደርቡ በሰፊ ግብ ልዩነት ባሸነፈበት ጨዋታ ግብ ማስቆጠር ችሏል። በሳምንቱ መጨረሻ ለሚጀመረው የአልባኒያ ሱፐርሊጋ እንዲረዳው ስኬንደርቡ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን እያደረገ ይገኛል።

ስኬንደርቡ 8 ግቦችን አስቆጥሮ ኬኤፍ አድሪያቲኩ ማሙራስ 8-0 አሸንፏል። የሁለተኛ ዲቪዚዮን ክለብ በሆነው ማሙራስ ላይ ቢኒያም በ79ኛው ደቂቃ ላይ ነው ግቡን ያስቆጠረው። ቢኒያም በነሃሴ ወር አልባንያ በሶስት አመት ውል ከተዛወረ በኃላ ክለቡ ከክሮሺያው ዳይናሞ ዛግሬብ ጋር ወደ ዮሮፓ ሊግ ምድብ ለመግባት በተደረገው ጨዋታ ተጠባባቂ ነበር።

የአልባኒያ ሱፐርሊጋ በሳምንቱ መጨረሻ ሲጀመር ኮርሲ ከተማ ላይ ስኬንደርቡ በሜዳው ኬኤስ ፍላሙታሪ ቭሎሪን ያስተናግዳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *