ሰላም ዘርአይ የኢትዮዽያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆና ተመረጠች

በ2018 በዩራጋይ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ከ17 አመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት አስቀድሞ የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ ያወጣው የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከቀናት መዘግየት በኋላ ስሟ በተደጋጋሚ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ተያይዞ ሲነሳ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ የሴቶች ቡድን ዋና አሰልጣኝ አሰልጣኝ ሰላም ዘርአይን የኢትዮዽያ ከ17 አመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።

በቅርቡ ኢንስትራክተር መሆኗ የተነገረላት አሰልጣኝ ሰላም በተጨዋችነት ዘመን ለትውልድህን አገልግል ፣ ለሀይኮፍ ያገለገለች ሲሆን በኋላም የቅዱስ ጊዮርጊስ የተስፋ ቡድን አሰልጣኝነት ስትሆን በመቀጠል ቅዱስ ጊዮርጊስ የሴቶች ቡድን ካቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ክለቡን በአሰልጣኝነት እየመራች ትገኛለች፡፡ በአሁኑ ሰአትም ወደ ሞሮኮ በማቅናት የአሰልጣኞች ስልጠና እየወሰደች መሆኑ ይታወቃል።

አሰልጣኝ ሰላም በቅርቡ አብረዋት የሚሰሩትን የስታፍ አባላት እና ተጨዋቾችን ምርጫ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮጵያ ከ ኬንያ ጋር የምታደርገው የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታ ጥቅምት ወር መጀመርያ ላይ አዲስ አበባ የሚካሄድ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *