​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለወዳጅነት ጨዋታ ወደ ቦትስዋና ያመራሉ

ቦትስዋና ከእንግሊዝ ቀኝ አገዛዝ ነጻ የወጣችበትን 51ኛ አመት በአል ምክንያት በማድረግ ሀገሪቱ ኢትዮጵያን ለወዳጅነት ጨዋታ መጋበዟን ተከትሎ በመጪው እሁድ የሁለቱ ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ 

የብሔራዊ ቡድኑ ልኡክ በመጪው ሀሙስ ወደ ስፍራኽ ሲጓዝ ሙሉ የትራንስፖርት እና የሆቴል ወጪ በቦትስዋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንደሚሸፈን ታውቋል፡፡ ፌዴሬሽኑም በአጭር ጊዜም ቢሆን ቡድኑን አቀናጅቶ ለጨዋታ ብቁ በማድረግ ወደ ስፍራው እንደሚያመራ አስታውቋል።

በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ከዚህ ቀደም በሱዳን የደርሶ መልስ ጨዋታ በድምር ውጤት 2ለ1 ተሸንፎ ከ2018ቱ የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና (ቻን) ከተሰናበተ በኋላ የነጥብም ሆነ የወዳጅነት ጨዋታ ያላደረገ ሲሆን የፊታችን እሁድ ወደ ቦትስዋና አምርቶ የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል። አሰልጣኝ አሸናፊ ለተጨዋቾች ጥሪ አቅርበው ዛሬ ልምምዳቸውን የጀመሩ ሲሆን በአብዛኛው የቡድኑ ስብስብ በቻን የማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ የነበሩ ተጨዋቾች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል። ከአሰልጣኙ ጋር በተያዘ ዜናም አሰልጣኙ በስራቸው እንዲቀጥሉ መወሰኑ ታውቋል።

በየአመቱ መስከረም 20 የሚከበረው የቦትስዋና የነጻነት በአልን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች ግብዣ እየቀረበላቸው ከሀገሪቱ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚጫወቱ ሲሆን በ2007 ዋልያዎቹ በቀረበላቸቸው ግብዘዣ መሰረት ወደ ስፍራው አቅንተው በስዩም ተስፋዬ (2) እና ዳዊት ፍቃዱ ጎሎች 3-2 አሸንፈው መመለሳቸው የሚታወስ ነው፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *