​ድሬዳዋ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ድሬዳዋ ከተማ ጋናዊው አጥቂ ክዋሜ አትራምን አስፈርሟል፡፡,

የ28 አመቱ አጥቂ የእግርኳስ ህይወቱን በጋናው ትልቅ ክለብ አሻንቲ ኮቶኮ የጀመረ ሲሆን ከ2009 እስከ 2016 ድረስ በግብፁ ዋዲ ዴግላ፣ በታይላንዱ ቲኦቲ ፣ በቬትናሙ ሀ ኖይ ቲ ኤንድ ቲ፣ በደቡብ አፍሪካዎቹ ብላክ ስዋሎውስ፣ ሚላኖ ዩናይትድ እንዲሁም በዲ.ሪ. ኮንጎው ስፖርቲቭ ባዛኖ ተጫውቶ አሳልፏል፡፡ ከ2016 አንስቶ ድሬዳዋ እስካመራበት ጊዜ ደግሞ በዛምቢያው ዛናኮ ሲጫወት ቆይቷል፡፡

የአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ቡድን በአጥቂ ስፍራ ላይ በክረምቱ የከፍተኛ ሊጉ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ዘካርያስ ፍቅሬ እና የናሽናል ሴሜንቱ መሐመድ ጀማልን ያስፈረመ ሲሆን ለአንድ አመት አስፈርሞት ከነበረው ጋናዊው ጌዲዮን አካክፖ ጋር ተለያይቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *