በዝውውር መስኮቱ እስካሁን አዲስ ተጫዋች ያላስፈረመው ደደቢት ዛሬ የ5 ተጫዋቾቹን ኮንትራት አድሷል፡፡ ደደቢት ዛሬ ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ሳምሶን ጥላሁን ፣ ሽመክት ጉግሳ ፣ ዳዊት ፍቃዱ ፣ አክሊሉ አየነው እና ብርሃኑ ቦጋለ ናቸው፡፡
ደደቢት ለተጫዋቾቹ ውል ማደሻ ምን ያህል ገንዘብ እንደከፈለ ማወቅ ባይቻልም ከክለቡ ባገኘነው መረጃ መሰረት ክለቡ ለተጫዋቾቹ ያወጣው ገንዘብ በወቅታዊው የገብያው ዋጋ መሰረት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ክለቡ ነገ ኮንትራቱን ማደሱን እንደሚቀጥልና የጋናዊዎቹን አዳሙ ሞሃመድ እና ጋብሬል አህመድ ኮንትራት እንደሚያድስና ከሌሎች ክለቦች ተጫዋቾችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡