ባንክ ቢንያም አሰፋ እና ፍቅረየሱስን አስፈርሟል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቡናው ቢንያም አሰፋ እና የኤሌክትሪኩ አማካይ ፍቅረየሱስ ተክለብርንን አስፈርሟል፡፡ ባንክ ለተጫዋቾቹ ፊርማ ምንያህል ወጪ እንዳወጣ ከክለቡ ማረጋገጫ አልተሰጠም፡፡

ቢንያም አሰፋ አምና ከኢትዮጵያውያን አጥቂዎች በሊጉ ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ አጥቂ ሲሆን ለቡና ውሉን ለማደስ የጠየቀው ገንዘብ በክለቡ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ቡናን ለቆ በሳምንቱ መጨረሻ ለሃምራዊዎቹ መፈረሙ ተነግሯል፡፡ ቢንያም ከዚህ ቀደም በ2004 እና 2005 ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጫውቷል፡፡ ወንጂ ስኳር ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሰበታ ከነማ ሌሎች ቢንያም የተጫወተባቸው ክለቦች ናቸው፡፡

የኤሌክትሪኩ አማካይ ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን በመጨረሻም ለባንክ ፈርሟል፡፡ ተጫዋቹ ለኤሌክትሪክ ኮንትራቱን ለማደስ ቢስማማም ባንክም ተጫዋቹን ለማዘዋወር መስማማቱ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር፡፡ በመጨረሻም ባንክ ፍቅረየሱስን ፌዴሬሽን ወስዶ ማስፈረም በእጁ ማስገባቱን ማረጋገጡ ተነግሯል፡፡

ባንክ እስካሁን ቶክ ጄምስ ፣ ቢንያም አሰፋ ፣ ፌቮ ኢማኑኤል ፣ አንተነህ ገ/ክርስቶስ ፣ ዳኛቸው በቀለ ፣ አምሃ በለጠ ፣ እና ፍቅረየሱስን ሲያስፈርም ጫላ ድሪባ እና አለምነህ ግርማን አሰናብቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *