​አጫጭር ዜናዎች፡ ሀሙስ ህዳር 7 ቀን 2010

ሴካፋ 

በሴካፋ ሲኒየር ቻሌንጅ ካፕ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከአሰልጣኝ አባላቶቹ ጋር በመሆን ተጨዋቾች የመመልመል ስራ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ህዳር 24 ለሚጀመረው ውድድር በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ምርጫው ተጠናቆ ወደ ዝግጅት እንደሚገቡም ሰምተናል፡፡ (ዳንኤል መስፍን) 


ፋሲል ከተማ

ፋሲል ከተማ የሴቶች ቡድን በኢትዮዽያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ተሳታፊ መሆኑን ተከትሎ 30 ተጨዋቾችን መልምሎ የመረጠ ሲሆን ዛሬ ባወጣው የአሰልጣኝ ቅጥር መስፈርት መሰረት አሰልጣኝ ተስፋሁን እሸቴን በዋና አሰልጣኝነት ሾሟል፡፡ ቡድኑን ከመመስረት አንስቶ በዝግጅት ወቅት ቡድኑን ሲያሰለጥን የነበረው አሰልጣኝ መካሻው አለም ም/አሰልጣኝ ሆኖ ሲሾም እና የቡድን መሪ በመሆን እንዲመራም ተመርጧል፡፡ የፋሲል ከተማ የሴቶች ቡድን የመጀመርያ ጨዋታውን ሰኞ በአአ ስታድየም ከወጣቶች አካዳሚ ጋር የሚያደርግ ይሆናል። (ዳንኤል መስፍን)


አክሊሉ አያናው 

ለሁለት ክለብ በመፈረሙ ምክንያት ለቅጣት ተዳርጎ የነበረውና ኋላ ላይ ቅጣቱ የተነሳለት ፤ ቆይቶ ደግሞ በድጋሚ እንዲተይ የተወሰነበት አክሊሉ አየነው ጉዳይ በመጨረሻም እልባት አግኝቷል፡፡ ፌዴሬሽኑ ተጫዋቹን መጫወት የሚፈልግበትን ክለብ እንዲመርት በወሰነው ውሳኔ መሰረት አክሊሉ ለኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት ምርጫው አድርጓል፡፡  ስራ አስፈፃሚዎች

የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ አባለት ከጠቅላላ ጉባኤው በኋላ የመጀመርያ ስብሰባቸውን ነገ ያደርጋሉ፡፡ በተለያዮ የሀሳብ ልዩነቶች ውስጥ እንደሚገኙ እና እንደተከፋፈሉ የሚነገረው የስራ አስፈፃሚ አባላት ነገ በሚያደርጉት መደበኛ ስብሰባቸው ምንም መቋጫ ሳይበጅለት ስብሰባው በመበተኑ ምክንያት ብዙ ሲያነጋግር በቆየው የምርጫው አጠቃላይ ሁኔታ ዋና አጀንዳቸው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። (ዳንኤል መስፍን)


አአ ከተማ ዋንጫ

የአአ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከአአ ሲቲ ካፕ ክለቦች በፐርሰት የሚያገኙትን ገቢ በቅርቡ ለየክለቦቹ በየደረጃው አከፋፍሎ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ እና እስካሁንም የዘገየው ከወጪ ቀሪ ያለውን የገንዘብ መጠን ለማስተካከል ጊዜ ስለሚፈልግ እንደሆነ ተገልፆል።

በተያያዘ ዜና አአ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን በዋናነት በሴቶች እና በወንዶች የሚያወዳድራቸው የውስጥ ውድድሮችን ለመጀመር ቅድመ ሁኔታዎች የጀመረ ሲሆን ህዳር ወር መጨረሻ ላይ ውድድሮቹን ለመጀመር እንዳሰበ ሰምተናል። (ዳንኤል መስፍን)ኦሮሚያ ዋንጫ

በኦሮሚያ ዳኞች እና ኮሚሽነሮች ማህበር አዘጋጅነት ከህዳር 5 – 15 ድረስ በዱከም ከተማ አስተናጋጅነት በአምስት ቡድኖች መካከል የሚካሄደው የኦርምያ የአንደኛ ሊግ ቡድኖች የዋንጫ ጨዋታ ባለፈው ማክሰኞ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምሯል፡፡ በመክፈቻው ጨዋታ ዱከም ከተማ ገላን ከተማን 2-1 ሲያሸንፍ ቢሸፍቱ ከተማ መተሀራ ስኳርን 2-0 ረቷል፡፡  ውድድሩ ዛሬ በአንድ ጨዋታ ሲቀጥል ቢሸፍቱ ከተማ ሆለታ ከተማን 1-0 አሸንፏል። ውድድሩ በዙር የሚካሄድ ሲሆን በአጠቃላይ ውጤት የተሻለ ነጥብ ያስመዘገበ ቡድን የውድድሩ አሸናፊ እንደሚሆን ታውቋል። (ዳንኤል መስፍን)


በአምላክ ተሰማ

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ በአምላክ ተሰማ በሞሮኮ አስተናጋጅነት በሚካሄደው  የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ጨዋታዎችን እንዲመሩ በካፍ ከተመረጡ ዳኞች መካከል ሆኗል፡፡ በአምላክ ስኬታማ ጊዜ እያሳለፈ በሚገኝበት በዚህ አመት የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ፣ የአለም ከ17 አመት በታች ዋንጫ ጨዋታዎች እና የአለም ዋንጫ ማጣርያዎችን መርቷል፡፡


ሲዳማ ቡና

የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ለማቋቋም ማሰቡን አስታውቋል፡፡ “ደጋፊ ማህበሩን በሚገባ ከማቋቋምም ባለፈ በተጠናከረ መልኩ ለማደራጀት ነው ሀሳባችን፡፡ በቅርቡም ወደ ስራ እነገባለን፡፡ ›› ብለዋል የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ መንግስቱ ሳሳሞ፡፡ (ቴዎድሮስ ታከለ)
መርሃ ግብሮች

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ – 3ኛ ሳምንት 

ቅዳሜ ህዳር 9 ቀን 2010

09:00 ወልዋሎ ዓ/ዩ ከ ሲዳማ ቡና (አዲግራት)

09:00 ወልዲያ ከ ድሬዳዋ ከተማ (ወልዲያ)

11:30 ኢትዮጵያ ቡና ከ መከላከያ (አአ)

እሁድ ህዳር 10 ቀን 2010

09:00 አርባምንጭ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ (አርባምንጭ)

09:00 ጅማ አባ ጅፋር ከ ፋሲል ከተማ (ጅማ)

09:00 ደደቢት ከ ሀዋሳ ከተማ (አአ)

09:00 ወላይታ ድቻ ከ አዳማ ከተማ (ሶዶ)

11:30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቀለ ከተማ (አአ)


ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ

ቅዳሜ ህዳር 09 2010

09:00 ባህርዳር ከተማ ከ አክሱም ከተማ (ባህርዳር)

09:00 ሽረ እንዳስላሴ ከ ኢትዮጵያ መድን (ሽረ)

እሁድ ህዳር 10 2010 

10:00 አማራ ውሃ ስራ ከ ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን (ባህርዳር)

09:00 የካ ክ/ከተማ ከ ሰበታ ከተማ (አዲስ አበባ)


ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዝዮን – 2ኛ ሳምንት

ቅዳሜ ህዳር 9 ቀን 2010

09፡00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ መከላከያ (አአ ስታድየም)

እሁድ ህዳር 10 ቀን 2010

09፡00 ጌዲኦ ዲላ ከ አዳማ ከተማ (ዲላ)

09፡00 ሀዋሳ ከተማ ከ ደደቢት (ሀዋሳ)

09፡00 ሲዳማ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ (ይርጋለም)

ማክሰኞ ህዳር 12 ቀን 2010

11፡00 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አአ ስታድየም)


ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 2ኛ ዲቪዝዮን – አንደኛ ሳምንት

እሁድ ህዳር 10 ቀን 2010

09፡00 ጥረት ኮርፖሬት ከ ሻሸመኔ ከተማ (ባህርዳር)

09፡00 ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ከ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ (አሰላ)

ሰኞ ህዳር 11 ቀን 2010

09፡00 ኢ/ወ/ስ/ አካዳሚ ከ ፋሲል ከተማ (አአ ስታድየም)

11፡00 ቂርቆስ ክፍለከተማ ከ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ (አአ ስታድየም)

ማክሰኞ ህዳር 12 ቀን 2010 

09፡00 ልደታ ክ/ከተማ ከ አአ ከተማ (አአ ስታድየም)

09፡00 አርባምንጭ ከተማ ከ ቦሌ ክፍለከተማ (አርባምንጭ)

ረቡዕ ህዳር 13 ቀን 2010

09፡00 ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ከ ኢትዮጵያ ቡና (አአ ስታድየም)


አፍሪካ

ሴካፋ ሙሉ መርሀ ግብር

ከህዳር 24 ጀምሮ በኬንያ አስተናጋጅነት የሚደረገው የሴካፋ ዋንጫ ድልድል ዛሬ ረፋድ ወጥቷል፡፡ 

የምድብ ድልድል

ምድብ አንድ

ኬንያ ፣ ሩዋንዳ ፣ ሊቢያ ፣ ታንዛኒያ ፣ ዛንዚባር

ምድብ ሁለት

ዩጋንዳ ፣ ዚምባቡዌ ፣ ቡሩንዲ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ደቡብ ሱዳን

የኢትዮጵያ ጨዋታዎች

ሰኞ ህዳር 25 ቀን 2010

ቡሩንዲ ከ ኢትዮጵያ (8፡00)

ዓርብ ህዳር 29 ቀን 2010

ደቡብ ሱዳን ከ ኢትዮጵያ (8፡00)

እሁድ ታህሳስ 1 ቀን 2010

ኢትዮጵያ ከ ዩጋንዳ (10፡00)

ማክሰኞ ታህሳስ 3 ቀን 2010

ዚምባቡዌ ከ ኢትዮጵያ (10፡00)

ሙሉ መርሀ ግብር


የአለም ዋንጫ ቋት

በሩስያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ፊፋ 32ቱን ሀገራት በ8 ቋቶች ከፋፍሏል፡፡ ፊፋ ቋቶቹን ያወጣው ሀገራቱ በፊፋ ሰንጠረዥ ባላቸው የብሔራዊ ቡድኖች ወቅታዊ ደረጃ መሰረት ሲሆን የአፍሪካ ሀገራትም በ3ኛ (ቱኒዚያ ፣ ግብፅ ፣ ሴኔጋል) እና 4ኛ (ናይጄርያ ፣ ሞሮኮ) ቋቶች ውስጥ ተመድበዋል፡፡


የቻን ቋት

የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) የእጣ ማውጣት ስነስርአት በነገው እለት በሞሮኮ ይካሄዳል፡፡ የአዘጋጅ ኮሚቴው ትላንት ባደረገው ስብሰባም ሀገራቶቹን በአራት ቋቶች ከፋፍሎ ይፋ አድርጓል፡፡ ከምስራቅ አፍሪካ በውድድሩ ላይ የሚካፈሉ ሱዳን ፣ ዩጋንዳ እና ሩዋንዳም በ3ኛው ቋት ላይ ተደልድለዋል፡፡

ቋት 1 – ሞሮኮ ፣ አንጎላ ፣ ኮትዲቯር ፣ ሊቢያ

ቋት 2 – ካሜሩን ፣ ጊኒ ፣ ናይጄርያ ፣ ዛምቢያ

ቋት 3 – ኮንጎ ዲ.ሪ. ፣ ዩጋንዳ ፣ ሩዋንዳ ፣ ሱዳን 

ቋት 4 – ቡርኪና ፋሶ ፣ ኢኳቶርያል ጊኒ ፣ ሞሪታንያ ፣ ናሚቢያ


ኮሳፋ 

የደቡባዊ አፍሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ኮሳፋ) የሚያዘጋጀው የኮሳፋ ከ20 አመት በታች ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ እንድትካፈል ጥሪ ቀርቦላት የነበረ ቢሆንም ምላሽ ባለመስጠቷ የማትካፈል ይሆናል፡፡    

የምድብ ድልድሉ ይህንን ይመስላል፡-


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *