​ጅማ አባጅፋር ቅጣት ተላለፈበት

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጅማ አባጅፋር ሀዋሳ ከተማን አስተናግዶ 2-0 ማሸነፉ ይታወሳል።

በጨዋታው ላይ የመጀመሪያ ግብ በተቆጠረበት ወቅት ከክለቡ ማመላለሻ አውቶብስ ረዳት ድንጋይ በመወርወር በረዳት ዳኛው ሸዋንግዛው ተባበል ላይ ጉዳት በማድረሱ እና ጨዋታው ለ13 ደቂቃዎች እንዲቋረጥ በማድረጉ ፣ በእለቱም የክለቡ ደጋፊዎች የፌዴሬሽኑን ስም እየጠሩ በመዝለፍ እና የሀዋሳ ከተማ አመራሮች እና ተጫዋቾችን በማስፈራራት እና ስብዕና የሚነካ ስድብ በመሰንዘራቸው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የእለቱን የዳኞች እና የኮሚሽነሩን ሪፖርት ከተመለከተ በኋላ እንደሚከተለው ውሳኔ ሰጥቷል።

1.ጅማ አባ ጅፋር በቀጣይ በሜዳው የሚያደርገውን ሁለት ጨዋታዎች ከከተማው 150 ኪሎ ሜትር ርቆ እንዲጫወት ተወስኗል። ውድድሩ የሚካሄድበት ቦታ እና ቀንም በሊግ ኮሚቴው ይወሰናል።

2. 150 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍል እና በ15 ቀናት ውስጥ ለፌዴሬሽኑ ገቢ እንዲያደርግ፡፡

3. ክለቡ ለደጋፊዎቹ የስፖርታዊ ጨዋነት ግንዛቤ በማስጨበጥ ለፌዴሬሽኑ ሪፖርት እንዲያደርግ የሚሉ ናቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *