ሊዲያ ታፈሰ በዓለም ከ20 አመት በታች ሴቶች ዋንጫ ጨዋታዎች ትዳኛለች

ኢንተርናሽናል አርቢቴር ሊዲያ ታፈሰ በፈረንሳይ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የዓለም ከ20 አመት በታች ሴቶች ዋንጫ ላይ ጨዋታዎችን ከሚመሩ ዳኞች መካከል ተካታለች።

የ2008 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ዳኛ ሊዲያ ባለፉት ተከታታይ አህጉራዊ እና አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ የመዳኘት እድል አግኝታለች። ከዚህ ቀደም የዓለም ሴቶች ዋንጫ እና የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ጨዋታዎችን መምራት የቻለች ሲሆን አሁን ደግሞ በነሐሴ ወር በፈረንሳይ በሚካሄደው የዓለም ከ20 አመት በታች ሴቶች ዋንጫ ላይም የምትመራ ይሆናል። ሊዲያ ከ2 አመት በፊት በተካሄደው የጆርዳን ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ዓለም ዋንጫ ላይም በተመሳሳይ ጨዋታዎችን መምራቷ የሚታወስ ነው።