ወንድወሰን ገረመው ከቡድን መሪ እና ተጫዋች ጋር በፈጠረው ግጭት ከካምፕ ተባረረ

የወላይታ ድቻው ግብ ጠባቂ ወንድወሰን ገረመው ከቡድን መሪው እና ከተጨዋቾች ጋር በፈጠረው ግጭት ከተጫዋቾች ማረፊያ እንዲወጣ ተደረገ

የወላይት ድቻ በዕለተ ረቡዕ የልምምድ መርሀግበሩ ላይ በነበረው ለሁለት ተከፍሎ በሚደረግ ጨዋታ ላይ ግብጠባቂው ወንድወሰን ገረመው ከበዛብህ መለዮ ጋር በፈጠሩት አለመግባባት መነሻነት በመሀከላቸው በተፈጠረ ግብግብ ለማገላገል የገባውን የቡድን መሪውን ሐብታሙን ደብድበሀል በሚል የክለቡ አመራሮች ወንድወሰን ገረመውን ከተጨዋቾች ማረፊያ እንዲወጣ ወስነዋል ። በዚህም መሰረት ግብ ጠባቂው በአሁን ሰዓት ከቡድኑ ጋር ተለያይቶ አዲስ አበባ ይገኛል። በክለቡ የአንድ ዓመት እገዳ እንደተላለፈበትም ተሰምቷል።

” በጨዋታ መሀል የተሰጠውን ቅጣት ምት ይገኛል እሱን ለመምታ ቦታ ሳስተካክል ሰዓት ለማባከን መስሎት ያሬድ ኃይለ ቃል ይናገረኛል ። በዚህ ተከፍቼ ከእርሱ ጋር እየተጋጨው የቡድን መሪው ሐብታሙ እንደ ቡድን መሪነቱ ሁሉንም ተጨዋች በኩል አይን ከማየት ይልቅ ክብረ ነክ ነገር ሲናገረኝ ከእርሱ ጋር ተጋጨው። ከዛ ከካምፕ እንድወጣ ተደረግኩ። አንድ ቀን ሆቴል አድሬ እቃዬን ይዤ አሁን አዲስ አበባ መጥቻለው። ” ያለው ወንድወሰን አንድ ዓመት ስለመቀጣቱ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ እና ደብዳቤ እንዳልደረሰው ተናግሯል።

የክለቡ አመራሮች በዚህ ጉዳይ ላይ ለማናገር ያደረግነው ጥረት ያልተሳካ ሲሆን በቀጣይ የሚሰጡንን ምላሽ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።