የተቋረጡ ውድድሮች የሚጀመርባቸው ቀናት ታውቀዋል

በትላንትናው እለት በጁፒተር ሆቴል በእግርኳስ ፌዴሬሽኑ እና የዳኞችና ታዛቢዎች ማኅበር መካከል በተደረገው ስብሰባ የተቋረጡ ውድድሮችን ለመጀመር ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል። በዚህም መሠረት ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አወዳዳሪነት የሚደረጉ ጨዋታዎች እንደሚደረጉ የተገለፀ ሲሆን ውድድሮቹ የሚጀምሩባቸው ጊዜያትም ተገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግንቦት 6 እና 10 በሚደረጉ የተስተካካይ መርሀ ግብሮች የሚጀምር ሲሆን የ23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከተስተካካይ መርሀ ግብር በኋላ የሚቀጥሉ ይሆናል። የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ደግሞ እሁድ ግንቦት 12 እንደሚጀምር ሲገለፅ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተስካካይነት ተይዘው የ18ኛ ሳምንት መርሀ ግብር የሚካሄድ ይሆናል።

የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ረቡዕ ግንቦት 8 ሲጀመር የ17 እና 20 ዓመት በታች ደግሞ ግንቦት 11 እና 12 እንደሚጀመሩ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።