ቦባን ዚሩንቱሳ አንድም ጨዋታ ሳያደርግ ኢትዮጵያ ቡናን ለቋል

በሁለተኛው ዙር ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው የአጥቂ አማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ቦባን ዚሩንቱሳ ጥሩ ግልጋሎት ያበረክታል ተብሎ ቢጠበቅም አንድም የነጥብ ጨዋታ ሳያደርግ ክለቡን ለቋል።

ዩጋንዳዊው የ28 ዓመቱ የቀድሞው ፖልኩዋኔ ሲቲ አማካይ ቦባን ከዚህ ቀደም የወረቀት ጉዳዮች ባለመጠናቀቃቸው ጨዋታ ማድረግ እንዳልቻለ ሲገለፅ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ በልምምድ ወቅት ያሳየው ብቃት የቡድኑን አሰልጣኝ እንዳላስደሰተ እና ለቡድኑ የተለየ ነገር ያበረክታል ተብሎ ስላልታመነበት ውሉ ሳያልቅ በስምምነት ሊለያዩ ችለዋል

በተያያዘ አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜስ ባሳለፍነው ቅዳሜ በካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ሩዋንዳ ላይ የሩዋንዳው ክለብ ራዮን ስፖርት ከኬንያው ጎር ማሂያ ጋር 1 ለ 1 የተለያዩበት ጨዋታ በስፍራው ተገኝተው መከታተላቸው እና በእንቅስቃሴያቸው የተማረኩባቸው ሦስት ተጫዋቾችን ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ቡና ለማምጣት እንደተስማሙም ተሰምቷል፡፡