አዳማ ከተማ ፎርፌ ተወሰነለት

በኢትዮጵያ ፕሪምየር በሲዳማ ቡና እና አዳማ ከተማ መካከል በተደረገው የ24ኛ ሳምንት ጨዋታ ሲዳማ ቡና 1-0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

በ23ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ባደረጉት ጨዋታ አዲስ ግደይ በ5 ቢጫ ምክንያት በጨዋታው ላይ መሰለፍ የለበትም የሚል ክስ ሀዋሳዎች ማስመዝገባቸው የሚታወስ ሲሆን አዲስ ግደይ ከሀዋሳው ጨዋታ በተጨማሪ ከአዳማ ጋርም ተሰላፊ ሆኖ ራሱ ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ ሲዳማ ቡናን አሸናፊ አድርጎት ነበር። ሆኖም ፌዴሬሽኑ ክሱን አሁን ተመልክቶ ተገቢ መሆኑን በማረጋገጥ አዳማ ከተማ በፎርፌ የ3-0 አሸናፊ እንዲሆን ወስኗል።

በዚህም መሰረት አዳማ ከተማ ነጥቡን ወደ 42 ከፍ በማድረግ እና ከጅማ አባ ጅፋርን ብዙ ባገባ በሚለው ህግ በመብለጥ 1ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።