ፋሲል ከድር ኩሊባሊን ለማስፈረም ተስማምቷል

ፋሲል ከተማ ኮትዲቫራዊው ከድር ኩሊባሊን ሲያስፈርም የአብዱራህማን ሙባረክን ውል አድሷል፡፡

በደደቢት በመሀል ተከላካይነት እና በአማካይ ስፍራ በመሰለፍ ባለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት ወጥ አቋም ያሳየው ከድር ኩሊባሊ በሁለት ዓመት ውል ክለቡን ለመቀላቀል የተስማማ ሲሆን የውጪ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሲከፈት ፊርማውን እንደሚያኖር ክለቡ ገልጿል።

ከአዳዲስ ተጫዋቾች ጎን ለጎን የነባሮችን ውል እያደሰ የሚገኘው ፋሲል የአጥቂው አብዱራህማን ሙባረክን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት አራዝሟል፡፡