ወላይታ ድቻ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርሟል

ወላይታ ድቻ ፀጋዬ አበራን የግሉ በማድረግ የክለቡ አራተኛ ፈራሚ አድርጓል፡፡

በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት በንቃት መሳተፍ የጀመረው ወላይታ ድቻ ኄኖክ ኢሳይያስ፣ ሳምሶን ቆልቻ እና ታሪክ ጌትነትን ዝውውር ያጠናቀቀ ሲሆን አሁን ደግሞ ፀጋዬ አበራን የግሉ አድርጓል። ተጫዋቹ በጦና ንቦቹ ቤት ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የሚቆይ ይሆናል።

በአርባምንጭ ከተማ በ2007 ወደ ዋናው ቡድን ያደገው ፀጋዬ በሶስት ዓመታት ቆይታው በተለያዩ ሚናዎች ላይ ግልጋሎት የሰጠ ሲሆን በመስመር፣ በአማካይ እና አጥቂ ስፍራዎች ላይ መጫወት የሚችል ሁለገብ ተጫዋች ነው።