የሀዋሳ ሴንትራል ዋንጫ ነገ ይጀመራል

የሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል ስፖንሰር ያደረገውና በ6 ክለቦች መካከል የሚደረገው ውድድር ‹ ሀዋሳ ሴንትራል ዋንጫ ›› በሚል ስያሜ ነገ ይጀመራል፡፡

ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2008 በሀዋሳ ስታድየም የሚደረገው ውድድር ውዝግቦች ያስተናገደ ሲሆን የሀዋሳ ከተማ ውድድሩን ማዘጋጀት ከዚህ ቀደም ውድድሩን ሲያደርግ በቆየው የደቡብ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እግርኳስ ፌዴሬሽን መካከል ውዝግብ ተነስቷል፡፡

የደቡብ እግርኳስ ፌዴሬሽን በብሄራዊ ሊጉ ውድድር ሀላባ ከነማን ለመደገፍ ወደ ድሬዳዋ ሲጓዙ ህይወታቸው ያለፉትን እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ለማሰብ በሚል ውድድሩን በ5 የፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ፣ በ2 የብሄራዊ ሊግ ክለቦች እና በአንድ ከክልሉ ውጪ በሚገኝ ተጋባዥ ክለብ አማካኝነት ለማካሄድ አስቦ የነበረ ቢሆንም ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ደግሞ የስታድየሙን እድሳተር በማስመልከት የ6 ክለቦች ውድድር አዘጋጅቷል፡፡

ዛሬ በወጣው የምድብ ድልድል መሰረት ስድስቱ ክለቦች በሁለት ምድብ ተከፍለዋል፡፡

ምድብ 1

ሲዳማ ቡና

ሆሳእና ከነማ

ወላይታ ድቻ

 

ምድብ 2

አርባምንጭ ከነማ

ድሬዳዋ ከነማ

ሀዋሳ ከነማ

 

ነገ የሚጀመረው ውድድር በመክፈቻው ሲዳማ ቡና ከወላይታ ድቻ በ8፡00 ላይ ጨዋታቸውን ሲያደርጉ በ10፡00 ላይ አርባምንጭ ከነማ ከ ሀዋሳ ከነማ ይጫወታሉ፡፡

ይህ የሴንትራል ካፕ መካሄዱን ተከትሎ የፕሪሚየር ሊጉ 14 ቡድኖች ከሊጉ መጀመር በፊት ውድድር ለማካሄድ አስችሏቸዋል፡፡ 6 ቡድኖች በሴንትራል ካፕ ሲሳተፉ ቀሪዎቹ 8 ቡድኖች ደግሞ መስከረም 22 በተጀመረው የአዲስ አበባ አምበር ዋንጫ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *