ብሄራዊ ቡድናችን ወደ ቀጣዩ የማጣርያ ዙር አልፏል

2018 በሩስያ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ስታዲየም ሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔን አስተናግዶ 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በመጀመሪው ጨዋታ 1ለ0 የተሸነፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጨዋታው በፊት ውጤቱን ይቀለብሳል ወይ የሚል ጥያቄ ቢበዛበትም ብሄራዊ ቡድኑ በሙሉ የጨዋታ ብልጫ የዛሬውን ጨዋታ አሸንፎዋል፡፡

4-1-3-2 የጨዋታ አቀራረብ ይዘው የገቡት አሰልጣኝ ዩሀንስ ሳህሌ በመጀመርያው ጨዋታ የተጠቀሙበትን ቡድ ይዘው ገብተዋል፡፡ ቋሚ አሰላለፉ የሚከተለውን ይመስል፡-

ታሪኬ ጌትነት

ስዩም ተስፋዪ አስቻለው ታመነ አንተነህ ተስፋዪ ተካልኝ ደጀኔ

ጋቶች ፓኖም

ራምኬል ሎክ ሽመልሽ በቀለ ኤፍሬም አሻሞ

ዳዊት ፍቃዱ በረከት ይሳቅ

IMG_6107

በጨዋታው ላይ ቡድኑ ሙሉ ለሙሉ የማጥቃት አጨዋወትን ሲተገብር ተስተውሎዋል፡፡ ገና ጨዋታው እንደተጀመረም ዳዊት ፍቃዱ ግብ አስቆጥሮ ኢትዮጵያ 1-0 እንድትመራ አስችሏል፡፡ ግቧ ቡድኑ ላይ የመነሳሳት አቅም የመጨመር ሀይል ነበራት፡፡

ከግቡ መቆጠር በኋላ ባሉት ደቂዎች በርካታ የግብ እድሎችን የፈጠሩ ቢሆንም ተጨማሪ ግብ ሳያስቆጥሩ ለእረፍት 1-0 ወጥተዋል፡፡

ከእረፍት መልስ ዋልያዎቹ በርካታ ያለቀላቸው የግብ እድሎች በተፈጠሩት የማጥቃት እንቅስቃሴ የታጀቡ ሲሆን በ48ኛው ደቂቃ በሳኦቶሜ የግብ ክልል በእጅ በመነካቱ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ወደ ግብነት ቀይሮ ኢትዮጵያ በድምር ውጤት 2-1 መሪ እንድትሆን አስችሏታል፡፡ በ74ኛው ደቂቃ ደግሞ ዳዊት ወደ ግብ ሲመታ ግብ ጠባቂው የመለሰውን ኳስ ተጠቅሞ ራምኬል ሎክ የእለቱን የማሳረግያ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በጨዋታው ሂደቶች ላይ የነበረው የቡድናችን የማጥቃት አጨዋወት ብዙ ስታዲየም የሚገኙ ተመልካቾችን ቢያስደስትም የተገኙትን በርካታ የግብ እድሎች አለመጠቀማቸው ላይ አንዳንዶቹ ጥያቄም ሲያነሱ ተስተውለዋል፡፡

በጨዋታው ላይ ጥሩ የሚባል አቆዋሙን ሲያሳይ የነበረው ሽመልስ በቀለ (በተለይ በመጀመሪያው 45) ቡድኑ እንዲያሸንፍ ከፍተኛ ሚና ነበረው፡፡ በ15ኛው ደቂቃ ላይ በጉዳት የወጣውን ተካልኝ ደጀኔን ተክቶ ወደ ሜዳ የገባው ብሩክ ቃልቦሬ ምንም እንኳን ተፈጥሯዊ የመስመር ተከላካይ ባይሆንም በተጠባባቂ ወንበር ላይ ሌላ የመስመር ተከላካይ ባለመኖሩ አሰልጣኝ ዮሃንስ በአማካይ ተከላካይ ሚና የሚታወቀውን ብሩክ ቃልቦሬን ለመጠቀም ተገደዋል፡፡

ኢትዮጵያ ጨዋታውን 3-0 ማሸነፏን ተከትሎ በአጠቃላይ ውጤት 3-1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ የቅድመ ማጣርያ ዙር አልፋለች፡፡ በቀጣ የማጣርያ ዙር ሪፑብሊክ ኦፍ ኮንጎን (ኮንጎ ብራዛቪል) የምትገጥም ሲሆን ይህንን ማጣርያ ካለፈች 20 ሃገራት ለሚካፈሉበት የምድብ ማጣርያ ትበቃለች፡፡

IMG_6275

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *