መቐለ 70 እንደርታ ጋናዊ ተከላካይ አስፈረመ

የመጀመርያው ዙር ፕሪምየር ሊጉን በመሪነት ያጠናቀቁት እና ስብስባቸው ለማጠናከር በሂደት ላይ የሚገኙት ምዓም አናብስት በመጀመርያው ዙር በተከላካይ መስመር የነበራቸው ጠባብ አማራጭን ለማስፋት ጋናዊው የመሃል ተከላካይ ክዌክ ኢንዶህን አስፈርመዋል።

በመሃል ተከላካይነት እና በመስመር ተከላካይነት መጫወት የሚችለው ይህ የቀድሞ የበርኩም ቼልሲ፣ ኸርትስ ኦፍ ኦክ እና ኸርትስ ላየን ተጫዋች ከሁለት ዓመት የደደቢት ቆይታ በኃላ ወደ ሌላው የመቐለ ከተማ ክለብ መቐለ 70 እንደርታ ተቀላቅሏል። በጋና ከ 23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ጨምሮ በሌሎች ታችኞች የብሄራዊ ቡድን እርከኖችም መጫወት የቻለው እና በዚ ዓመት ከዳዊት ወርቁ እና ኤፍሬም ጌታቸው በመፈራረቅ የደደቢትን ተከላካይ ክፍል የመራው ይህ የ28 ዓመት ተጫዋች በጉዳት ምክንያት ለሳሳው የመቐለ 70 እንደርታ ተከላካይ ክፍል ጥሩ አማራጭ ያሆናል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *