በኢትዮጵያ ቡና ጠቀቅላላ ጉባኤ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ በድጋሚ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል

ኢትዮጵያ ቡና ትላንት በኔክሰስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የ2007 የበጀት አመት ሪፖርት እና የ2008 የውድድር ዘመን እቅድ የቀረበ ሲሆን ለቀጣዮቹ አመታት ቡናን የሚመሩ ስራ አስፈፃሚዎች ምርጫም ተደርጓል፡፡

በክለቡ ስራ አስኪያጅ እና የጉባኤው ምክትል ሰብሳቢ አቶ ገዘኸኝ ወልዱ የቀረበው የ2007 ክንውኖች ሪፖርት በቴክኒክ ፣ ገበያ መምሪያ እና ፕሮሞሽን እንዲሁም ፋይናንስ እና አስተዳደር በሚሉ ርእሶች የተከፋፈሉ ሲሆን በቴክኒካዊ ጉዳዮች ዙርያ የቡድኑ የማሸነፍ ፍላጎት ፣ የማበረታታት እና የማነሳሳት ፣ የክለቡን ስም እና ዝና የማስጠበቅ ፣ ወጥ የሆነ ቋሚ 11 አለመኖር ፣ አላማ የለሽነት ፣ በእያንዳንዱ ጨዋታ በመረጃ የተመረኮዘ ሪፖርት አለመኖር እና የአጨዋወት ባህሉን መልቀቅ የመሳሰሉ ችግሮች እንደነበሩ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ ለነዚህ ችግሮች መፍትሄ ለማበጀትም ትላልቅ ውሳኔዎች መወሰናቸው በሪፖርቱ ላይ ተካትቷል፡፡

በውጭ ኦዲተሮች ሂሳብ እንዲመረመር ፣ የተጫዋቾች መኖርያ ካም በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ እና የተጫዋቾች ውል በሰው ሃይል አስተዳደሩ ዳታ ውስጥ እንዲካተት መደረጉ በ2007 ከተከናወኑ ክንውኖች መካከል በሪፖርቱ የተጠቀሱ ናቸው፡፡

በአዳማ ከተማ በተደረገ የጎዳና ላይ ባዛር ፣ በኤግዝቢሽን ማእከል በተደረገ ባዛር በመሳተፍ ፣ የክለቡን አርማ ከያዙ ቁሳቁሶች ሽያጭ ፣ ከወርሃዊ መፅሄት እንዲሁም በኢትዮጵያ ክለቦች የመጀመርያ የሆነው የሬድዮ ፕሮግራምን በመጀመር 5.12 ሚልዮን ብር ገቢ መገኘቱን ሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡

የ2008 እቅዶች

በአቶ ገዘኸኝ ወልዴ ባቀረቡት የ2008 የስራ እቅድ ክለቡ ለማሳካት ካለማቸው ግቦች መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በሚሳተፊበት ውድድሮች የቻምፒዮንነት ክብር እንዲገናፀፉ ማድረግ፡፡

5 ተጫዋቾች ወደ ዋናው ቡድን ፣ 10 ተጫዋቾች ደግሞ ከ17 አመት በታች ቡድ ወደ 20 አመት በታች ቡድን ማሳደግ

ክለቡ የተረከበውን መሬት ለልምድ ሜዳ አመቺ እንዲሆን ማድረግ

የክለቡ ታላላቅ ግለሰቦችን ታሪክ የያዘ መፅሃፍ ማሳተም እና ስለ ክለቡ የተዜሙ መዝሙሮችን ሰብስቦ በአዲስ መልክ ማሰራት፡፡

ከተለያዩ ዘርፎች አምና ከተገኙ ገቢዎች የላቀ ገቢ ማስገባት እና የመሳሰሉ እቅዶች ተጠቅሰዋል፡፡

ሂሳብ

የቡናን የ2007 ሂሳብ የመረመረው የውጭ ኦዲተር ባቀረበው ሪፖር መሰረት ክለቡ በአጠቃላይ 18.6 ሚልዮን ብር ገቢ ሲያስገባ ከነዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው ከቡና ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ ክለቡ ያገኘው 11 ሚልዮን ነው፡፡

በዚሁ አመት ክለቡ 19.5 ሚልዮን ብር ወጪ አድርጓል፡፡ ከዚህም ውስጥ ለተጫዋቾች ፊርማ እና ደሞዝ የወጣው 11 ሚልዮን ብር የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡

በሪፖርቱ መሰረት ክለቡ በአጠቃላይ ከአንድ ሚልዮን ብር በላይ ኪሳራ አስተናግዷል፡፡

IMG_3925

በሪፖርት እና እቅድ እንዲሁም በተሳታዎች ውይይት ረጅም ሰአት የወሰደው ጠቅላላ ጉባኤ የተጠናቀቀው የቦርድ አመራሮችን በመምረጥ ነው፡፡ በተደረገው ምርጫ መሰረትም የክለቡ የረጅም ጊዜ የበርድ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ በድጋሚ ክለቡን በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠዋል፡፡ ከቡና አብቃዮች የተወከሉት አቶ መኩርያ መርጊያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሲመረጡ ስራ አስኪያጁ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ የቦርዱ ፀሃፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *