በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ንግድ ባንክ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

– ቅድስተ ማርያም በድንቅ እንቅስቃሴ ኤሌክትሪክን አሸንፏል

ዛሬ በተደረጉ ኢትዮጵያ ሴቶች ማእከላዊ ሰሜን ዞን 2ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ቅድስተ ማርያም ውድድር ዘመናቸውን የመጀመርያ ድል አሳክተዋል፡፡

በ9፡00 ዳሽን ቢራን ያስተናገደው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2-0 አሸንፏል፡፡ ለባንክ ሁለቱን የድል ግቦች ከመረብ ሳረፉት ሽታዬ ሲሳይ በ24ኛው እና ረሒማ ዘርጋ በ54ኛው ደቂቃ ናቸው፡፡ በመክፈቻው በደደቢት 2-1 የተረታው የአምናው ቻምፒዮን ንግድ ባንክ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል፡፡

በ11፡30 የተጀመረው የኤሌክትሪክ እና ቅድስተ ማርያም ጨዋታ በቅድስተ ማርያም 5-2 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ሀት-ትሪክ የሰራችው መዲና አወል ጎልታ በወጣችበት ጨዋታ ቅድስተ ማርያሞች ተመልካቹን ያስገረመ ድንቅ እንቅስቃሴ አሳይተዋል፡፡

ኤሌክትሪኮች በፅዮን ፈየራ 11ኛው ደቂቃ እና በአይናለም ጸጋዬ የ30ኛ ደቂቃ የፍፁም ቅጣት ምት ግብ 2-0 መምራት ቢችሉም ዮርዳኖስ በርሄ እና መዲና አወል በ39 እና 41ኛ ደቂቃዎች ባስቆጠሯቸው ግቦች 2-2 በሆነ ውጠቴት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

ከእረፍት መልስ ሙሉ የጨዋታ ብልጫ ያሳዩት ቅድስተ ማርያሞች ተጨማሪ ሶስት ግቦች በመዲና አወል (70 እና 88ኛው ደቂቃ) እና እየሩሳሌም በነበሩ (76) አስቆጥረው ጨዋታው 5-2 ተጠናቋል፡፡

የደረጃ ሰንጠረዡን ደደቢት እና መከላከያ በ6 ነጥቦች ሲመሩ ንግድ ባንክ ፣ ቅድስተ ማርያም ፣ ዳሽን ቢራ ፣ ልደታ እና ኢትዮጵያ ቡና በ3 ነጥቦች ይዘዋል፡፡ እቴጌ እና ኤሌክትሪክ ደግሞ ሁለቱንም ቸዋታ የተሸነፉ ቡድኖች ናቸው፡፡

የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን የቅድስተ ማርያሟ መዲና አወል በ5 ግቦች ስትመራ የቅዱስ ጊዮርጊሶቹ ሔለን ሰይፉ እና ትመር ጠንክር በ2 ግቦች ይከተላሉ፡፡

 

የ2ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ውጤት

ሙገር 1-2 መከላከያ

ኤሌክትሪክ 2-5 ቅድስተ ማርያም

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2-0 ዳሽን ቢራ

ኢትዮጵያ ቡና 0-7 ደደቢት

እቴጌ 0-2 ልደታ

 

የ3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች

እሁድ ህዳር 26/2008

ደደቢት ከ እቴጌ (09፡00 አአ)

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሙገር (11፡30 አአ)

ማክሰኞ ህዳር 28/2008

ቅድስተ ማርያም ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (09፡00 አአ)

መከላከያ ከ ኤሌክትሪክ (11፡30 አአ)

ሀሙስ ህዳር 30/2008

ዳሽን ከ ኢትዮጵያ ቡና (09፡00 ጎንደር)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *