ኢትዮጵያ ዋንጫ | ድቻ በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፍ ጅማዎች ወደ ልምምድ አልተመለሱም

በኢትዮጵያ ዋንጫ የመጀመርያ ዙር ወላይታ ድቻ ወደ በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡ ተጋጣሚ የነበረው ጅማ አባ ጅፋር ተጫዋቾች በበኩላቸው ዛሬም ልምምድ አልሰሩም።

የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋቾች ከደመወዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ ያለፉትን ሁለት ቀናት ልምምድ ማቆማቸውን ተከትሎ ነገ ለሚደረገው ጨዋታ ወደ ሶዶ ያላመሩ ሲሆን ፌዴሬሽኑም ወላይታ ድቻ የፎርፌ አሸናፊ ሆኖ እንዲያልፍ ወስኗል።

በተያያዘም የጅማ አባጅፍር ተጫዋቾች የደመወዝ ጥያቄ በማንሳት ከመቐለው ጨዋታ በኋላ ልምምድ ያልሰሩ ሲሆን ዛሬም በልምምድ ሜዳ ሳይገኙ እንደቀሩ ለማወቅ ተችሏል። ጉዳዩ በጊዜ እልባት የማይሰጠው ከሆነ የም ለ27ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ወደ ወላይታ ሶዶ ላያቀኑ እንደሚችሉ ከክለቡ አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡