ቻን 2016 – ካሜሩን ከዩጋንዳ አቻ ተለያየች

 

በአፍሪካ ሃገራት ዋንጫ (ቻን) በምድብ ሁለት ከኢትዮጵያ፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና አንጎላ ጋር የተመደበችው ካሜሩን ዛሬ ቀትር ላይ ከሴካፋ ሻምፒዮኗ ዩጋንዳ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቃለች፡፡

በዩጋንዳ እግርኳስ ማህበር (ፉፋ) የቴክኒክ ማዕከል በተደረገው የሁለቱ ሃገራት ጨዋታ 0-0 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

ጨዋታው የተከታተለው ዩጋንዳዊው ስፖርት ጋዜጠኛ ፍሬድ ሙአምቡ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጠው አስተያየት ካሜሩን ጠንካራ ቡድን እንደሆነ ገልጿል፡፡ “በጣም ጠንካሮች እና በተክለ ሰውነት ግዙፎች ናቸው፡፡ በፈጣን መልሶ ማጥቃት የተጋጣሚ ብድንን መረበሽ ተመራጭ አጨዋወት ምርጫቸው ነው፡፡ የመከላከል አደረጃጀታቸውም ጥሩ ነው፡፡”

የማይበገሩት አንበሶቹ የቻን ዋንጫ የምድብ ጨዋታቸውን ዕሁድ አንጎላን በመግጠም የሚጀምሩ ይሆናል፡፡

 

ፎቶ – ዩጋንዳ ራድዮ ኔትዎርክ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *