የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ከዛሬው ጨዋታ ውጭ ሆነ

የቻን 2020 ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታውን ከጅቡቲ ጋር ዛሬ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበሉ አስቻለው ታመነን በጉዳት ምክንያት አይጠቀምም።

አስቻለው ድሬዳዋ ቡድኑ ዝግጅት ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በጉልበቱ ላይ ባጋጠመው መጠነኛ ጉዳት ህክምናዎችን በመከታተል ቢቆይም ህመሙ ምንም ዓይነት መሻሻል ሊያሳይ ባለመቻሉ ነው ከዛሬው የጅቡቲ የመልስ ጨዋታ ውጭ መሆኑ የተረጋገጠው።

አሰልጣኝ አብርሐም መብራቱ በአስቻለው ታመነ ምትክ ምን አልባት ደስታ ደሙን የሚጠቀሙ መሆኑ ሲነገር በአምበልነት ድርሻውን ደግሞ አማኑኤል ዮሐንስ በመረከብ ቡድኑን እየመራ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡