በክልል ክለቦች ሻምፒዮና ለፍፃሜ የደረሱ ቡድኖች ታውቀዋል

በአዳማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተካሂደው መከላከያ እና ሀሳሳ ከተማ ለፍፃሜ የሚያበቃቸውን ድል አስመዝግበዋል።

07:00 መከላከያ ከ ሾኔ ከተማ ያደረጉት የመጀመርያ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 0-0 በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት አምርተው መከላከያ 4-2 በማሸነፍ ለፍፃሜ ዋንጫ ጨዋታ አልፏል። ከሀገር መከላከያ ሠራዊት የተውጣጡ ተጫዋቾችን ብቻ የያዘው መከላከያ በሩብ ፍፃሜው ሐውዜን ከተማን 3-0 ሲያሸንፍ ሾኔ ከተማን በአንፃሩ ደጋን ከተማን 2-1 አሸንፎ ነበር ለዛሬው የግማሽ ፍፃሜ መድረስ የቻሉት።

09:00 የጀመረው ሌላኛው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ሀሳሳ ከተማን ከኣብዲ ሱሉልታ አገናኝቶ ከጠንካራ ፉክክር በኋላ ሀሳሳ ከተማ 2-1 አሸንፏል። የተከተል ነጋልኝ ሁለት ጎሎች አሳሳን ለፍፃሜ ዋንጫ ሲያደርስ የኦብዲ ሱሉልታን ብቸኛ የማስተዛዘኛ ጎል ተመስገን ወዳጄ አስቆጥሯል።

ሀሳሳ ከተማ ከኤጀሬ ከተማ ጋር አንድ አቻ በመውጣታቸው በመለያ ምት አሳሳ ከተማ 4-3 አሸንፎ ግማሽ ፍፃሜውን ሲቀላቀል ኣብዲ ሱሉልታዎች ፍራውን ከተማን 1-0 በማሸነፍ ነበር ለግማሽ ፍፃሜው መድረስ የቻሉት።

በ36 ቡድኖች መካከል በብዙ አስገራሚ ክስተቶች ታጅቦ ለ16 ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ክልል/ከተማ አስተዳደር ክለቦች ሻምፒዮና ሐሙስ ነሐሴ 2 ቀን 2011 የሚጠናቀቅ ይሆናል።

03:00 | ኣብዲ ሱሉልታ ከ ሾኔ ከተማ (ደረጃ)
08:00 | መከላከያ ከ አሳሳ ከተማ (ፍፃሜ)


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡