ወልቂጤ ሁለት ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

በፕሪምየር ሊጉ የመጀመርያ ተሳትፎውን ለማድረግ እየተዘጋጀ የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ አቡድለጢፍ ሙራድ እና ዳግም ንጉሴን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል።

በመስመር አጥቂነት የሚጫወተው አብዱለጢፍ ሙራድ በአራዳ ክፍለ ከተማ፣ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ፣ ሀዲያ ሆሳዕና ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን የተጠናቀቀው የውድድር ዘመንን በኢትዮጵያ መድን በስኬት በማሳለፍ 13 ጎሎችን በከፍተኛ ሊጉ ማስቆጠር ችሏል።

የተከላካይ ስፍራ ላይ ተጫዋቹ ዳግም ንጉሴ ሌላኛው ወልቂጤን በአንድ ዓመት የተቀላቀለ ተጫዋች ሆኗል። ተጫዋቹ በሀላባ ከተማ፣ ወላይታ ድቻ እና ኢኮስኮ እንዲሁም የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በሲዳማ ቡና አሳልፏል።

አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ከሊጉ ክለቦች ቀዳሚ የሆነው ወልቂጤ ከተማ እስካሁን የዛሬዎቹን ጨምሮ ሰባት ተጫዋቾችን አስፈርሟል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡