ድሬዳዋ ከተማ የተከላካዩን ውል አራዘመ

ለቀጣይ ዓመት ውድድር የነባር ተጫዋቾቹን ውል በማራዘም ላይ ትኩረት ያደረገው ድሬዳዋ ከተማ የዘነበ ከበድን ውል አራዝሟል።

በዘንድሮ የውድድር ዓመት ቡድኑ ጋር መልካም ጊዜ ያሳለፉት ግብጠባቂው ሳምሶን አሰፋ እና ተከላካዩ አንተነህ ተስፋዬን ውል ለተጨማሪ ዓመት ያራዘሙት አሰልጣኝ ስምዖን ዓባይ አሁን ደግሞ የቀኝ መስመር ተከላካያቸውን ዘነበ ከበደን ለተጨማሪ አንድ ዓመት የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት አስፈርመውታል። ዘነበ ከዚህ ቀደም ከሙገር ሲሚንቶ ተስፋ ቡድን አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን የተጫወተ ሲሆን በመቀጠል ሀዋሳ ከተማ፣ ደደቢት እና ሲዳማ ቡና የተጫወተባቸው ክለቦች ናቸው።

በሌላ ዜና አሰልጣኝ ስምዖን ዓባይ በቀጣይ ቀናት በለቀቁባቸው ተጫዋቾች ምትክ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ እንደሚያመጡ ሰምተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡