በክቡር ይድነቃቸው ተሰማ የመታሰቢያ ውድድር የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቀዋል

14ኛው የክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የመታሰቢያ የታዳጊዎች ውድድር የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ሲጠናቀቁ የግማሽ ፍፃሜ ኃላፊ አራት ቡድኖች ተለይተው ታውቀዋል።   

በተፈጥሮ ያገኙት ችሎታ እንዳለ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ እያስመለከተን የሚገኘው የታዳጊዎቹ ከ15 ዓመት በታች ውድድር ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ተሻግሮ ዛሬ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ተካሂደዋል። ያለፉት ሦስት ቀናት ውጤቶቹም የሚከተሉት ናቸው፡-


የአራተኛ ቀን ውጤቶች

አሰላ ፍሬ 2-2 ጫካ ሜዳ
ፉትቦል ላይፍ 0-1 ጫጫ
መካኒሳ 4-1 አዲስ ከተማ
ተስፋ ለኢትዮጵያ 0-1 አዳማ ብሩህ ተስፋ

አምስተኛ ቀን ውጤቶች

ቤተሰብ 0-0 አብዲ ቦሩ
ታቦት ማደሪያ 3-1 ሳሪስ አዲስ ሰፈር
ጨው በረንዳ 5-1 ኮልፌ ፕሮጀክት
አንለያይም 0-2 ኤንፓ

የመጨረሻ ቀን ውጤቶች

ጫጫ 3-2 አሰላ ፍሬ
ጫካ ሜዳ 1-2 ፉትቦል ላይፍ
መካኒሳ 3-3 አዳማ ብሩህ ተስፋ
አዲስ ከተማ 1-2 ተስፋ ለኢትዮጵያ

ከምድብ አንድ አብዲ ቦሩ (7 ነጥብ) ፣ ከምድብ ሁለት ኤንፓ (9 ነጥብ)፣ ከምድብ ሦስት ጫጫ (9 ነጥብ) እና ከምድብ አራት አዳማ ብሩህ ተስፋ (7 ነጥብ) አንደኛ ሆነው በማጠናቀቅ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

በዚህም መሠረት በቀጣይ ሳምንት ለፍፃሜ ዋንጫ ለማለፍ

ማክሰኞ ነሐሴ 21 ቀን 2011

02:30 | አብዲ ቦሩ ከ ጫጫ
03:30 | ኤንፖ ከ አዳማ ብሩህ ተስፋ

የፍፃሜ ጨዋታ ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን ተካሂዶ የውድድሩ ፍፃሜ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡