ሴካፋ ከ15 ዓመት በታች| ብሩንዲ ማለፏን ስታረጋግጥ ኤርትራ እና ሶማሊያ አቻ ተለያይተዋል

በኤርትራ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘውና ዘጠነኛ ቀኑን የያዘው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ዋንጫ ዛሬም ሲቀጥል ብሩንዲ ሱዳንን አሸንፋ ማለፍዋ አረጋግጣለች። ኤርትራ እና ሶማሊያ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

በ8:00 ሰዓት የተጀመረው እና የሩዋንዳ ፍፁም ብልጫ የታየበት የሱዳን እና የሩዋንዳ ጨዋታ አራት ግቦች የታየበት ነበር። በጨዋታውም ሩዋንዳ በሙጊሻ አዳሙ፣ ኢንተይቴካ ፍሎሬን እና ኢተርቴካ ጃን ግቦች ታግዛ ሱዳንን አራት ለአንድ አሸንፋለች።
ይህን ተከትሎ ሩዋንድ ኬንያን ተከትላ ማለፍዋ ስታረጋግጥ ከምድቡም አዘጋጅዋ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ ከውድድሩ ውጭ መሆናቸው አረጋግጠዋል።

በ10:30 የጀመረው እና በዝናብ ታጅቦ የተካሄደው የአዘጋጇ ኤርትራ እና ሶማሊያ ነበር። ውጥረት የተሞላበት ነበር የተባለለት ጨዋታም አንድ ለ አንድ በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ውድድሩ ነገም ሲቀጥል በምድብ ለ የመጨረሻ ጨዋታዎች በ8:00 ሰዓት ኢትዮጵያ ከታንዛንያ እንዲሁም በ10:30 ሩዋንዳ እና ዩጋንዳ ይገናኛሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡