ከፍተኛ ሊግ | ቡታጅራ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

አስራት አባተን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው ቡታጅራ ከተማ የዝውውር እንቅስቃሴውን ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ በመቀላቀል ጀምሯል።

የቢሾፍቱ ከተማ እና የንግድ ባንክ የቀድሞ አማካይ አዲስ አስራት፣ የቀድሞው የቢሾፍቱ ከተማ እና መከላከያ ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች አማኑኤል ባርባ፣ ከባቱ ከተማ የመስመር ተከላካዩ አብዱልአዚዝ አማን፣ በዱከም ከተማ እና የካ ክ/ከተማ የተጫወተው የመስመር ተጫዋቹ በጋሻው ክንዴ፣ የቀድሞ ንግድ ባንክ እና በዘንድሮ አመት በናኖ ሁርቡ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ግዙፉ ግብ ጠባቂ ፋሪስ አለዊ እንዲሁም በዱከም ከተማ እና ቢሾፍቱ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ እያዩ ሲሳይ ወደ ቡድኑ የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸው።

ቡታጅራ ከተማ በ2012 የውድድር ዓመት ጠንካራ ሆኖ ለመቅረብ በተለያዩ ክለቦች የማሰልጠን ልምድ ያለው አሰልጣኝ አስራት አባተ መቅጠሩ የሚታወስ ሲሆን በቡድኑ የነበሩ 13 ተጫዋቾችን ውል ማደሱ የታወቀ ሲሆን በቅርቡም ሌሎች ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ እንደሚያካትቱ ተገልጿል ።


© ሶከር ኢትዮጵያ