ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ይመራሉ

የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ ሲከናወኑ ሉዋንዳ ላይ የሚደረገው ጨዋታም በኢትዮጵያ ዳኞች ይመራል።

የአንጎላው ፔትሮ አትሌቲኮ ሎዋንዳ እና በዩጋንዳው ኬሲሲኤ መካከል የሚደረገው ይህ ጨዋታ ሎዋንዳ ላይ በ12፡00 የሚካሄድ ሲሆን ጨዋታውንም በላይ ታደሰ በዋና ዳኝነት፣ ክንዴ ሙሴ እና ትግል ግዛው ደግሞ በረዳት ዳኝነት እንዲሁም ብሩክ የማነብርሃን በአራተኛ ዳኝነት እንዲመሩ እንዲሆኑ በካፍ ተመድበዋል።

በላይ ታደሰ በካፍ ቻምፒየንስ የመጀመርያ ዙር ማጣሪያ ላይ የሱዳኑ ኤል ሜሪክ ከ አልጀሪያው ጂኤስ ካባሊ ያደረጉትን የመልስ ጨዋታ መምራቱ የሚታወስ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ