ዑመድ ኡክሪ አዲስ ክለብ ተቀላቅሏል

ኢትዮጵያዊው አጥቂ ዑመድ ኡክሪ ከሁለት ዓመታት የስሞሃ ቆይታ በኃላ አስዋንን ተቀላቅሏል።

የሰሜን አበቦች በመባል የሚታወቁት እና በአሰልጣኝ ማግዲ ዓብዱል አቲ የሚሰለጥኑት አስዋኖች በዚህ የውድድር ዓመት ነው ወደ ዋናው የግብፅ ሊግ ያደጉት። በ2017 ከሊጉ የወረዱት አስዋኖች ከሁለት ዓመታት ቆይታ በኃላ የሊጉ ተሳታፊ ሆነው ይቀርባሉ። በውድድሩ ተፎካካሪ ለመሆን ከፈፀሟቸው ዝውውሮች መካከልም የዑመድ ኡኩሪ ዝውውር አንዱ ሆኗል።

ከዚህ ቀደም ለኤንፒ፣ አል ኢትሃድ አሌክሳንደርያ፣ ኤል ኢንታግ ኤል ሀርቢ እና ለሥሞሃ የተጫወተው ኢትዮጵያዊው አጥቂ በዚህ የውድድር ዓመት በአዲሱ ክለቡ መልያ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሽመልስ በቀለ የሚገኝበት ምስር አልማቃሳን በመግጠም ዓመቱን ይጀምራል።


© ሶከር ኢትዮጵያ