የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የምድብ ድልድል እንዴት ይሆናል?

ፌዴሬሽኑ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2012 የውድድር ዘመን 24 ቡድኖች በሁለት ምድብ ከፍሎ ማዋቀሩን ማሳወቁን ተከትሎ በቀጣይ የምድብ ድልድሉ ማንን ከማን ያገናኛል የሚለው ተጠባቂ ጉዳይ ሆኗል። 

ሶከር ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮቿ ባገኘችው መረጃ መሠረት የምድብ ድልድሉ ይሄንን በመሰለ መልኩ መካሄዱን ለማወቅ ተችሏል።

ምድብ ሀ

መቐለ 70 እንድርታ
ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጅማ አባጅፋር
መከላከያ
ወልዋሎ
ወላይታ ድቻ
ስሑል ሽረ
ደደቢት
ወልቂጤ ከተማ
ሀዲያ ሆሳዕና
ሰበታ ከተማ
ኢኮስኮ

ምድብ ለ

ሲዳማ ቡና
ፋሲል ከነማ
ሀዋሳ ከተማ
ባህርዳር ከተማ
ኢትዮጵያ ቡና
አዳማ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ
ደቡብ ፖሊስ
ለገጣፎ ለገዳዲ
ኢትዮጵያ መድን
አርባምንጭ ከተማ
ነቀምቴ ከተማ

በሁለት ምድብ በተከፈለው በዚህ ውድድር የምድቡ አሸናፊ የሆኑ ሁለት ቡድኖች በገለልተኛ ሜዳ በሁለት ዙር የፍፃሜ ጨዋታ ያደርጉና አሸናፊው ቡድን የውድድሩን ዋንጫ ከማንሳቱ ባሻገር ኢትዮጵያን በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሚወክል ሲሆን ሁለተኛ በመሆን የሚያጠናቅቀው ቡድን ደግሞ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ይወክላል። በአንጻሩ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ የሚሆነው ቡድን ኢትዮጵያን በሴካፋ ውድድር የሚወክል ይሆናል።

በሌላ ዜና በዘንድሮ ዓመት በሚካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚሳተፉ ክለቦች ከብሔር እና ማንነት ጋር ተያይዘው የሚጠሩት ለውጥ እንደሚደረግባቸው በመመስረቻ ረቂቅ ደንቡ ላይ ተጠቅሷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ