አዳነ ግርማ ወደ አዲስ አዳጊው ቡድን ለማምራት ተስማምቷል

አዲስ አዳጊው ወልቂጤ ከተማ አዳነ ግርማን ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል ስምምነት ላይ ሲደርስ ከተጫዋችነት በተጨማሪ ሌላ ሚና ሊሰጠው እንደሆነም ተገልጿል።

የእግር ኳስ ህይወቱን በሀዋሳ ከተማ የጀመረው አንጋፋው ሁለገብ ተጫዋች በቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታው የብቃቱ ጫፍ ላይ የደረሰ ሲሆን ለብሔራዊ ቡድንም ወሳኝ ግልጋሎት አበርክቷል። ተጫዋቹ ከአስር ዓመት የጊዮርጊስ ቆይታው በኋላ አምና ወደ ሀዋሳ ተመልሶ መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ በርካታ ተጫዋቾችን ወዳስፈረመው ወልቂጤ አምርቷል።

አዳነ በአዲሱ ቡድኑ ከተጫዋችነት በተጨማሪ ሌላ ሚና ሊሰጠው እንደሚችል ታማኝ ምንጮች ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል። ለአሰልጣኝ ደግአረገ ምክትል ለመቅጠር ተቃርቦ ከተመስገን ዳና ጋር ሳይስማማ የቀረው ክለቡ አዳነን የምክትል አሰልጣኝነት ሚና ሊሰጠው እንደሆነ ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ