ሴቶች ዝውውር | ድሬዳዋ ከተማ አስራ ሦስት ተጫዋቾች ሲያስፈርም የነባሮችንም ውል አድሷል

ድሬዳዋ ከተማዎች አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው በመቀላቀል ወደ ዝውውሩ ሲገቡ በክለቡ ቁልፍ ሚና የነበራቸው አስር ተጫዋቾችን ውልም አራዝመዋል፡፡

አሰልጣኝ ብዙዓየው ታደሰ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፀችው ዘንድሮ በክለቡ ውስጥ በርከት ያሉ ከተማው ያፈራቻቸው ተጫዋቾችን ለማሰባሰብ እቅድ በመያዝ እየተንቀሳቀሱ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ዝውውሮቹን ከመፈፀም ይልቅ በድሬዳዋ ውስጥ ካሉ የሴቶች ፕሮጀክት እስከ አምስት ተጫዋቾች ለማካተት ማሰቧን ገልጻለች።

አዳዲስ ከፈረሙት ውስጥ ተከላካይዋ ሀሳቤ ሙሶ በድጋሚ ከጥረት ኮርፖሬት ወደ ክለቡ ስትመለስ እታለም አመኑ (አማካይ ከሀዋሳ ከተማ)፣ ፀጋነሽ ወራና (አጥቂ ከአርባምንጭ)፣ ታደለች አብርሀም (አጥቂ ከንግድ ባንክ)፣ ቁምነገር ካሳ (አጥቂ ከጥረት ኮርፖሬት)፣ ማዕድን ሳህሉ (አማካይ ከጥረት ኮርፖሬት)፣ ቤተልሄም አሰፋ (አማካይ ከልደታ ክ/ከተማ)፣ ትብቃ ፋንታ (ግብ ጠባቂ ከጥረት ኮርፖሬት)፣ ዓይናለም ሽታ (ግብ ጠባቂ ከቂርቆስ ክ/ከተማ)፣ ማህደር ባዬ (ተከላካይ አ.አ ከተማ)፣ ፀሀይነሽ በቀለ  (ተከላካይ አርባምንጭ ከተማ)፣ ተዋበች ተስፋዬ (ተከላካይ ከሸመኔ ከተማ)፣ ነስማ አብደላ (ተከላካይ ከድሬዳዋ ከተማ ፕሮጀክት) ሌሎች አዳዲስ ፈራሚዎች ሆነዋል።

በክለቡ ነባር ከነበሩትና ውላቸውን ከተጠናቀቁት መካከል አስሩን በክለቡ ለማቆየት ውላቸው የተራዘመ ሲሆን ብዙሀን እንዳለ፣ ይመችሽ ዘመዴ፣ ስራ ይርዳው፣ አያና ሙሳ፣ ቤተልሄም ኪዳኔ፣ ሊና መሐመድ፣ ዕድላዊት ተመስገን፣ አያንቱ ውብዓለም፣ መቅደስ ተስፋዬ እና ሂሩት ደሴ በምስራቁ ክለብ ተጨማሪ ዓመት የሚቆዩ ተጫዋቾች ናቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ