ሴቶች ዝውውር| እመቤት አዲሱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ተቀላቀለች

ትላንት እና ከትላንት በስትያ ሰባት ተጨዋቾችን ያስፈረሙት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች እመቤት አዲሱን ከሰዓታት በፊት ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።
ከአርባ ምንጭ ከተማ ወደ መከላከያ ካመራች በኋላ ባለፉት ዓመታት በሴቶች እግርኳስ ጎልታ መውጣት የቻለችው እመቤት ስሟ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ቢያያዝም በመጨረሻ ማረፊያዋ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሆኗል። 

የተከላካይ አማካይዋ በወቅቱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጥሩ ግልጋሎት እየሰጡ ከሚገኙ ተጫዋቾች አንዷ ናት።


© ሶከር ኢትዮጵያ