የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን የውይይት መድረክ አዘጋጀ

በወቅታዊ የእግርኳሱ ውዝግብ ዙርያ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የሚገኙበት የውይይት መድረክ በኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን አማካኝነት አዘጋጅቷል።

የዘጠኙ የክልልና የ2ቱ ከተማ መስተዳድር እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንቶች፣ የስፖርት ኮሚሽን አመራሮች እና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች በተገኙበት በጋራ ለመነጋገር ማክሰኞ መስከረም 13 ቀን 2012 ከጠዋቱ 03:00 በስፖርት ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ የጋራ ስብሰባው ተዘጋጅቷል።

ለእግርኳስ መልካም ነገር ይዞ ይመጣል ተብሎ ተስፋ ከተደረገበት ከዚህ የውይይት መድረክ በኋላ ምናልባትም ኀሙስ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከክለቦች ጋር ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ሊይዝ እንደሆነ ሰምተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ